የህዳሴ ግድብን የውኃ ሙሌት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ
የግድቡ የብረታ ብረት ሥራ መቶ በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ
ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 24, 2020)፦ የህዳሴ ግድብን በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. ውኃ ለመሙላት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገና የግድቡ የብረታ ብረት ፍሬም ሥራ መቶ በመቶ መጠናቀቁን የታላቁ ህዳሴ ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂንየር ክፍሌ ሆሮ እንዳስታወቁት፤ በሐምሌ ወር በመጀመሪያው የውኃ ሙሌት ሥራ 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ውኃ የሚሞላ ሲሆን፤ ይህም ሁለት ተርባይነሮችን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የግድቡ የብረታ ብረት ሥራ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን፤ የሲቪል ሥራው 87 በመቶ፤ እንዲሁም የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው ደግሞ 46 በመቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል። (ኢዛ)



