በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው 10,736 ደርሰዋል
የጤና ሚኒስቴር
ባለፉት 24 ሰዓት 965 ተመርምረው ሁሉም ነፃ ኾነዋል
ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 23, 2020)፦ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረግ ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ በአጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺሕ በላይ ሲደርስ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 965 ሰዎች ተመርምረው አንድም የቫይረሱ ተጠቂ ሳይገኝ ቀርቷል።
የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓት ክንውኑን በማስመልከት ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 15 ቀን ባወጣው ሪፖርት፤ እስከዛሬ ድረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 10,736 ደርሷል። ከዚህ ውስጥ 965 ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የተደረገ ምርመራ ሲሆን፤ ውጤቱም ሁሉም ነፃ መኾናቸውን የሚያመላክት ኾኗል።
ይህም በመኾኑ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 116 ነው። ከዚህ ውስጥ እስከ ትናንት ድረስ 21ዱ ማገገማቸው መገለጹ ይታወሳል። (ኢዛ)



