FDRE Ministry of Education

ትምህርት ሚኒስቴር

የተማሪዎች ክፍያ ከ50-70 በመቶው ብቻ ይከፈል ተብሏል

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 21, 2020)፦ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሒደታቸውን ያቋረጡ ሲሆን፤ የግል ትምህርት ቤቶች ለሠራተኞቻቸው ከሚከፍሉት ደምወዝና ተማሪዎችን ክፍያ በተመለከተ ብዥታ ተፈጥሮ ቆይቷል።

ተማሪዎች ትምህርት ባቋረጡበት ሁኔታ ወርሃዊ የትምህርት ቤት ክፍያ በምን ሁኔታ መፈፀም አለበት በሚለው ላይ የተለያዩ አመለካከቶች ሲስተናገዱ የነበረ ሲሆን፤ ትናንት የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ የግል ትምህርት ቤቶች ማስከፈል የሚችሉት በቀደሙት ወራት ሲያስከፍሉ ከነበሩት ከ50-75 በመቶው ብቻ እንዲኾን፤ ለተማሪዎችም በተለያዩ መንገዶች ትምህርቱን ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸው መወሰኑን አስታውቋል።

ከዚህም ሌላ የግል ትምህርት ቤቶች ለሚያስተዳድሯቸው ሠራተኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ ደምወዛቸውን እንዲከፍሉ አስገዳጅ ውሳኔ መተላለፉንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ