የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ሚኒስቴር

84ቱ በለይቶ ማቆያ ሕክምና ላይ ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 18, 2020)፦ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ባላፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደርገላቸው 659 ሰዎች፤ ዘጠኝ አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች በመገኝታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 105 ደርሷል።

አዲስ በበሽታው መያዛቸው ከተገለጹት ውስጥ ስደስቱ ወንዶች ሲሆኑ፣ ሦስቱ ሴቶች ናቸው። ከዘጠኙ ውስጥ ስምንቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ አንዱ ደግሞ የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ሰው መኾኑ ተገልጿል።

ከ13 ዓመት እስከ 73 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እነዚህ አዲስ ተጠቂዎች መካከል የጅማ ነዋሪ የኾነቸው የ20 ዓመት ወጣት የተገኘች ሲሆን፤ አራቱ የአዲስ አበባ፣ ሦስቱ ደግሞ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ናቸው።

በድሬዳዋ ከተማ የተገኙት ሦስቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች፤ ከጅቡቲ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው።

በጅማ የተገኘችው ደግሞ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች ነች ተብሏል።

ዛሬ በወጣው መረጃ እስከአሁን ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥ 6890 ደርሷል። ከ105ቱ አጠቃላይ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 84ቱ በለይቶ ማቆያ ሕክምና ላይ ናቸው። 16ቱ ደግሞ ያገገሙ ሲሆን፣ በጽኑ ሕክምና ክፍል አንድ ሰው ይገኛል። ሕይወታቸው ያለፉት ሦስት መኾናቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ሁለቱ ጃፓናውያን ደግሞ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ