Addis Ababa Riverside Project

የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 2, 2019):- ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚጠይቅ የተነገረለትንና የአዲስ አበባን ገጽታ በመልካም ይቀይራል ተብሎ የሚጠበቀው “የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት” ትናንት በይፋ ተጀምሯል።

አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 56 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ነው። የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታውን በማሥጀመሩ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ “አዲስ” ለማድረግ በተገባው ቃል መሠረት ሥራው መጀመሩን ተናግረዋል።

በቻይና ድጋፍ የሚሠራው ይሄ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በስምንት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል። ይኸውም ግንቦት 2012 ዓ.ም. ሥራው የሚያልቅ መኾኑ ታውቋል።

ከወንዝ ደረጃ የማስዋብ ሥራው ባሻገር፤ ፕሮጀክቱ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ተጨማሪ ግንባታዎች ይኖሩታል። ይህ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ወጪው የሚሸፈነው በቻይና መንግሥት ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ የወንዝ ዳርቻ ልማት 12 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

ቀጣዮቹ የግንባታው ሥራዎችም በየደረጃው የሚቀጥሉ ሲሆን፣ ከተማዋ ከፍተኛ የቱሪዝም ገቢ የምታገኝበት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅና የከተማዋንም ገጽታ የሚቀይር ስለመሆኑ ተገልጧል። ከወንዝ ዳርቻ ልማቱ ሌላ ፕሮጀክቱ የኮንሰርት ማሳያ ስፍራ፣ ሰው ሠራሽ ኃይቆች፣ የተለያዩ የመዝናኛ ማዕከላትና የመሳሰሉት ግንባታዎችን ያካትተ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ