• ”እንዲህ ያለ የምርጫ ውጤት በአምባገነኖች ብቻ የሚካሄድ ነው፤ ውጤቱ በሠላማዊ ትግል የሚያምኑትን ሲያኮማሽሽ፣ በትጥቅ ትግል የሚያምኑትን ያበረታታል፤ በዚህም ምክንያት ጦርነት በአካባቢው ቢጀመር ለዓለምም ሆነ ለአካባቢው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ሊያስከትል ይችላል” አቶ ጀዋር መሐመድ (ተመራማሪ)
  • ”ህዝቡ መርጦናል” አቶ በረከት ስምዖን
  • ”መራጮች ወደ ምርጫ ሲሄዱ ከፍተኛ ጥልቀት ባለው ፍርሃት ተሸብበው እንደነበር ለመገመት አያስቸግርም” ሌስሊ ሌፍኮ (ኒዩማን ራይትስ ዎች)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም. May 27, 2010)፦ ዛሬ የአል ጀዚራ እንግሊዝኛ ቴሌቭዥን ጣቢያ የአቶ መለስ ዜናዊን ቀኝ እጅና የመንግሥት የኮምዩኒኬሽን ሚኒስትር የሆኑትን አቶ በረከትን፣ በግል ተመራማሪና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለአል ጀዚራ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት አቶ ጀዋር መሐመድን ከዋሽንግተን፣ እንዲሁም ከሂዩማን ራይትስ ዎች ሌስሊ ሌፍኮን ከዋሽንግተን በ”ኢንሳይድ ስቶሪ” ፕሮግራሙ ባለፈው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. የተካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ አነጋግሯቸዋል። (ሙሉውን ውይይት ለማየትና ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ