የሕወሓት ቀቢጸ ተስፋ የተጠናወተው የትግል ስልት ለምንና ለማን?

Amhara Region Prosperity Party

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ

ለትግራይ ሕዝብ ሲባል ሕወሓትን ያቀፈ የትግል ስልት መከተል ሆደ-ሰፊነት እንጂ ድንቁርና አይደለም። እስከአሁን በነበረው የትግል ጉዞ ሕወሓትን ከልክ በላይ መታገስ መስተዋሉ ተገቢና ትክክለኛ አቅጣጫ ነው። አሁንም ቢሆን ለትግራይ ሕዝብ ያልተመቸ ምንም አይነት ሁኔታ መከተል አያስፈልግም። የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት በፍጹም አንድ አይደሉም፤ አንድ ሆነውም አያውቁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሰላማዊና ሕጋዊ ትግል ያለን ታማኝነት በሐሰት ውንጀላ አይገታም!! - ባልደራስ

ባልደራስ

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝብ በተባበረ ትግል ጨቋኝ፣ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ-ዴሞክራሲ የነበረውን የሕወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ አስወግዶ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን መጠነ ሰፊ ትግል ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በዶ/ር ዐቢይ የሚመራው የኦዴፓ/ብልጽግና አመራር የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎት ከዳር ለማድረስ በአደባባይ ቃል ገብቶ ኃላፊነቱን መረከቡም ይታወሳል። ኾኖም ይህንን ወደ ነፃነትና ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ የሽግግር ጥያቄ በተገቢው ሁኔታ ለመመለስ በጣም አቅቶታል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በገሀድ እንደታየው የብልጽግና ፓርቲ እየተከተለ ያለው ፖለቲካ በተረኝነት መንፈስ የተቃኘ ነው። ለዚህም ነው ፓርቲው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማረጋጋትና፣ የሕዝቡን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበርና ብሔራዊ መግባባት ለማስፈን ያቃተው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያለበቂ ውይይት እና ግልጽነት በጎደለው መልኩ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለው ጥድፊያ በአስቸኳይ ይቁም! (ኢዜማ)

ኢዜማ

ገዢው ፓርቲ ያለበቂ ውይይት እና ግልጽነት በጎደለው መልኩ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለው ጥድፊያ በአስቸኳይ ይቁም!

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ

አንኳር

- ቴልኮም በ21ኛው ክፈለ ዘመን የፋይናንስ ሥርዓት መተግበሪያ፣ የመገናኛ ብዙኃን የደም ቧንቧ፣ ከፍተኛ የሆነ አገራዊና ወታደራዊ መረጃዎችን ማስተላለፍያ፣ ከመሪዎች ጀምሮ ከፍተኛ የአገር አስተዳደሪዎች መረጃ መቀባበያ፣ ለደህንነት ሥራዎች መረጃ ማግኛ ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጦር መሳሪያና ጦር ሜዳ ሆኖ ተመልከተናል። ከዚህ ባለፈ ኢንዱስቲሪው ብዙ ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች ተወዳደሪነታቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆነ ግብዓት እና ለአገራችን የወደፊት እድገት ያለውን አቅም መገነዝበ ተገቢ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቋም መግለጫ

ብልጽግና

ሕወሓት አሁንም የትግራይ ሕዝብ የለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ የቀድሞ የማታለል ሴራውን እየተገበረበት ይገኛል

እኛ የትግራይ ተወላጅ የሆንን የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣ ባለፉት ቀናት ስለአጠቃላይ የአዲስ አበባ የፓርቲያችን መዋቅር እንዲሁም ኮቪድ 19፣ የምርጫ መራዘምና የሕግ አማራጮች በሚል ርዕስ ስናደርግ የነበረውን ውይይት በማጠናቀቅ የሚከተለውን የጋራ አቋም መግለጫ አውጥተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከትግራይ ብልጽግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ

"ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ የተከሰተው ለአንድ ወጣት ክቡር ሕይወት ህልፈትና ለሁለት ወጣቶች የመቁሰል አደጋ በክልሉ ውስጥ የሰላምና ዲሞክራሲ እጦት ማሳያ ነው" የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ

ከሁሉ አስቀድመን በመቐለ ከተማ በጠራራ ፀሐይ ክልሉን እየገዛ ባለው ፓርቲ በታጠቁ ኃይሎች በጥይት ተደብድቦ በተገደለው ትግራዋይ ወጣት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰቦቹ ለወዳጆቹና ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ እንዲሁም ለሰላም ወዳድ የትግራይ ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳችን ሆኗል! (አብሮነት)

አብሮነት

ከአብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት (#አብሮነት) የተሰጠ መግለጫ

አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት (#አብሮነት) ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የተከሰተው “የለውጥ ሒደት” መሰረታዊ የአገሪቱን የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት በሚያስችል አግባብ ያልተካሄደና የከሸፈ መሆኑን በመገንዘብ አገሪቱን ወደ አንድ አዲስና ጤናማ የሽግግር ሒደት የሚያስገባ አማራጭ ሐሳብ በረቂቅ ደረጃ አዘጋጅቶ ለሕዝብ ውይይት ማቅረቡ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብን በሽግግር መንግሥትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያወጣው መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያወጣው መግለጫ

ለመላው የአማራ ሕዝብ፣
ለድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፣
ለመላው ኢትዮጵያውያን!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ አውዶችን በጥልቀት በመገምገም፤ የአማራ ሕዝብን ወቅታዊ አቋምና ዘላቂ ጥቅሞችን፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ኃይሎች ፍላጎቶችን እና የቀረቡ አማራጮችን በፅሞና በመመርመር፤ በዚህም መሠረት፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ