መድረክ ከቀልዱ ምርጫ ራሱን በማግለል፤ ቁም ነገር ይሥራ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሀብታሙ አሰፋ

ምርጫ 2002 አስቀድሞ በሂደቱ ተጭበርብሮ የቀረው የመጨረሻ ቀን ቴአትር ብቻ ነው። የቴአትሩ አዘጋጆች እና መሪ ተዋንያኑ የእነ አቶ መለስ ቡድን ያሰበው እንዲሳካ መታጀብ ይፈልጋል። የዚህ የተጭበረበረ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ሕገ ወጥ ሥራዎችን ሠርቷል። በዚህም ቀዳዳዎችን ሁሉ ደፍኜያለሁ ብሎ ይናገራል። ተደጋግሞ እንደተገለጸው የተደፈኑት ቀዳዳዎች የአፈና ሥርዓቱን በሥልጣን ለማቆየት የወጡ ሕገ ወጥ አዋጆችና ልዩ ልዩ እርምጃዎች ናቸው። አሸባሪው ”የፀረ-አሸባሪነት” አዋጅ ይቃወሙኛል ያላቸውን ሁሉ ለማፈን እየዋለ ነው። የፕሬስ ነፃነትን አደጋ ላይ ጥሏል። የአዲስ ነገር አዘጋጆችን መጨረሻ ልብ ይሏል። የነ ጄኔራል ተፈራ ማሞን የፈጠራ ክስ እና ሕገ ወጥ ውሳኔ ማንሳት ይበቃል። ምርጫውን በፈለገው መንገድ ለመቆጣጠር እንዲችል የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር የተቻለውን ሁሉ አድርጓል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቀልድ ምርጫ መሳተፍ ትርጉሙ ምንድነው?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይልማ በቀለ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

ውድ ወንድሜ አቶ ግርማ ካሣ ያቀረቡትን ጽሑፍ በአዲስ ቮይስ ድረ ገጽ ላይ አንብቤዋለሁ። አቶ ግርማ ካሣ በየጊዜው በዳያስፖራ ድረ ገፆች ላይ በአለው የሀገራችን ሁኔታ የሚጽፉትን ተከታትዬ አነበዋለሁ። ጊዜዎትን ወስደው፤ በጥሞና አስበው የሚያወጡት ጽሑፍ አንባቢዎች ስለ ውድ ሀገራችን እንድናስብ ያበረታታናል ብዬ አምናለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፊታችን ምርጫ ቀልድ ነው፤ መድረኩ ግን መሳተፉ ይበጀዋል

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

የ2002 ምርጫ ሊደረግ ከአንድ ወር በታች ቀርቶታል። ገዢው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ”ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲሆን ለማድረግ የነበረኝን ቁርጠኝነት እያሳየሁ ነው” ይላል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችም ምርጫውን ለመታዘብ አዲስ አበባ ገብተዋል። መድረኩ ባለፉት ሦስት ሣምንታት ብቻ በመቱ፣ በወልቂጤ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣ በኮምቦልቻ እንዲሁም በተለያዩ የአዲስ አበባ ወረዳዎች ታላላቅ ህዝባዊ ስብሰባዎችን እያደረገ ነው። በአቶ ኃይሉ ሻውል የሚመራው መኢአድ በአዋሳ፣ በአቶ ልደቱ የሚመራው ኢዴፓ ደግሞ በአለታ ወንዶ፣ ጎንደርና ባህር ዳር ህዝባዊ ስብሰባዎች ያደረገ ሲሆን፤ የምርጫ ዘመቻቸውን አጧጥፈውታል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ አቶ መለስ ማጅራቱን ከመቱት ምርጫ ተቃዋሚዎች ለምን ራሳቸውን አያገሉም?

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሀብታሙ አሰፋ

በምርጫ 97 የህዝብ ድምፅ ከተሰረቀ በኋላ ሥርዓቱ ያሰጉኛል ያላቸውን ሁሉ እያሳደደ ያጠቃ ነበር። ዳንኤል በቀለ “አክሽን ኤድ” የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከኃላፊዎቹ አንዱ ነው። በሙያው የሕግ ባለሙያም ጭምር ነው። ምርጫውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ከሚሰጡ ምሁራን አንዱ ነበር። ሃሳብን መግለፅ ወንጀል በመሆኑ የእነ አቶ መለስ ደህንነቶች ከሚያሳድዷቸው ዜጎች አንዱ ይሆናል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድብቅነት - ዘላፊነት - ቀጥሎስ?

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

መሣፍንት ዘፈረንሣይ ለጋሲዮን ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

“… አቶ ስየም እንዳሉት ሰው ከስህተቱም ሆነ ከስኬቱ ይማራል (እሳቸው የተማሩት ምን እንደሆነ ሲናገሩ አልሰማሁም እንጂ)። አሁን ባለው የሀገራችን ሁኔታ ከናንተ በላይ ከስህተት መማርን ማሳየት የነበረበት ማን ነበር? አሁንም ጊዜ ጥላችሁ አልሄደችም - ይቅርታ ለመጠየቅ በለበጣ ቀነ-ቀጠሮ ማስቀመጡን ትታችሁ፤ ህዝብ ፊት በመቆም የቆሸሸ እጃችሁን ታጠቡ። ማንነታችሁንም አደባባይ አውጡ። … ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢህአዲግ ልዑካኖች በርካታ ጥያቄዎችን ይዘው ተመለሱ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዘውገ ፋንታ ከስያትል

እሑድ አፕሪል 18 ቀን 2010 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ገዥ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በስያትል ተገኝተው፣ “ከባንክ የተቀመጠ ዕንቁ” ካሏቸው የኢትዮጵያ ወገኖች ጋር የኢትዮጵያን አስከፊ ሁናቴ አስመልክቶ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። መልስ ያልተገኘላቸውን ብዙ ጥያቄዎች ልዕካኖቹ ወደ ሀገራችን ይዘው ተመልሰዋል። ትዝብትን ያተረፈ ንግግር ግን ተንጸባርቋል። በጣም ሳይጋነን የምትታወስ ትንሽ የታሪክ ቀን ነበረች ማለት ይቻላል። ሙሉውን አስነብበኝ ...