0.6% ያገኙት ተቃዋሚዎች ናቸው ህወሓትን ያሸነፉት

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

0.6% ያገኙት፣ ግን 99.4% ያገኘውን ህወሓትን ያሸነፉት ተቃዋሚዎች ናቸው

ናኦሚ በጋሻው ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

”ምርጫ” ተደረገ ይሉናል። እኛ ግን ጨዋታና ቀልድ ነው የተደረገው እንላለን። ከምርጫው በፊት ይሄንኑ ነበር የምንናገረው። ምርጫ የሚወሰነው በድምፅ ሰጪው ሳይሆን በቆጣሪው ነው ስንል ነበር። መድረኩ ”ተሸነፈ” እንደሚባል ጥርጣሬ አልነበረንም። እንደገመትነውም እንደ ዶር መርራ ጉዲና፣ ኢንጂነር ግዛቸው፣ አቶ አንዱዋለም፣ አቶ ስየ አብርሃ የመሳሰሉ አንጋፋና ተወዳጅ የፖለቲካ መሪዎች፣ ተሸነፉ እየተባልን ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግልጽ ደብዳቤ - ለአቶ መለስ ዜናዊ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ይድረስ ለተከበሩ አቶ መለስ ዜናዊ

ተጻፈ ከግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

ምድረ አሜሪካ - ቺካጎ

በቅድሚያ ባሉበት ቦታ ለርስዎና ለቤተሰብዎ ሠላምታዬ ይድረስዎ!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አምላክ ሆኖ ሳለ እኛን ለማዳን ወደዚች ምድር መጣ። ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተወልዶ ሰው ሆነ። በምድር በሚመላለስበት ጊዜ እራሱን ሲጠራ ”የሰው ልጅ” ብሎ ነበር የሚጠራው። በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅትም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አንዱ ደቀ መዝሙሩን ሲያለቅሱ አይቶ፣ እናቱን ”አንቺ ሴት እንሆ ልጅሽ” ነበር ያላት። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ መለስ ዜናዊ፣ ለአቡነ ጳውሎስ፣ ...

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ከኮሎኔል አሥራት ቦጋለ

1. ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለወያኔ ድርጅት፣

2. ለአቡነ ጳውሎስ፣

3. በየጊዜው ከሚነፍሰው ነፋስ ጋር ለምትነፍሱ ብሌጣ-ብልጥ ሆድ-አደሮች፣

4. ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች፣

5. ለመለዮ ለባሹ ሠራዊት፣

6. ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ፣

ከሁሉ በማስቀደም በየአቅጣጫው ሁላችሁንም ከሚያጋጥማችሁ ስህተቶች እየተገታችሁ ወደ ቁምነገር በመመለስ በጎ በጎውን እንዲያሳስባችሁ እመኝላችኋለሁ። እውነት እንደሬት የምትመር እንደ ኮሶ የምታንገፈግፍ ስለሆነች ብዙ ጊዜ አቅራቢያዎቿን ትሰዋለች። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ ዋዜማ እንዲህ አለፈ… (እይታ- ከአዲስ አበባ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
ከአዲስ አበባ ወደ የክ/ሀገሩ ሸቀጣ ሸቀጦችን የሚያስጭኑ ነጋዴዎች ሥራቸውን አቁመዋል። በባንክ የነበራቸውን ገንዘብ በማውጣት በየቤታቸው አስቀምጠዋል። ምክንያቱ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ችግር ቢፈጠር ቅድሚያ ጥንቃቄ ለማድረግ ነው። አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከምርጫው ጋር በተያየዘ የአንዳንድ ተማሪዎችን የፈተና ጊዜ አራዝሟል። በዚህና ይሄን በመሰለው ምክንያት የ6ኪሎ ዩንቨርስቲ ምድረ-ግቢ ከሐሙስ ጀምሮ ፀጥ-ረጭ ብሏል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድርጅታዊ አቅም ሳይገነቡ ስሜታዊ እርምጃዎች መውሰድ ጉዳት አለው

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

በቅርቡ «ምርጫው ቀልድ ነው፤ መድረኩ ግን ቢሳተፍ ይበጀዋል» በሚል ርእስ ለአንባቢያን ባቀረብኩት ጽሁፍ ላይ ባነሳኋቸው አንዳንድ ነጥቦች ላይ፣ የማውቃቸውና የማክበራቸው ወዳጄ፣ አቶ ይልማ በቀለ የሰጡትን ምላሽ አነበብኩ። አቶ ይልማ በተለያዩ የአገራችን ጉዳዮች ላይ ትምህርት ሰጪ መጣጥፍት የሚያቀርቡ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ የዲሞክራሲ ታጋይ ናቸው። በዚህ አጋጣሚ ለሚያደርጉት አስተዋጾና ጥረት ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫውን አለመሳተፉ ጥቅም ላያመጣ ቢችልም ትልቅ ጉዳት ግን ይኖረዋል

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ናኦሚ በጋሻው ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

“ምርጫ ቀልድ ነው። መድረኩ ግን መሳተፉ ይበጀዋል” በሚል ርዕስ አቶ ግርማ ካሣ የጻፉትን መጣጥፍ ኢትዮሜዲያ ላይ ወጥቶ አነበበኩ። ርዕስ አመራረጣቸው የሚያስደንቅ ነው። ርዕሱን በመመልከት “ምን ማለታቸው ነው? ቀልድ ነው ብለው እንዴት ተሳተፉ ይላሉ” ብዬ ወዲያው ነበር ጽሑፉቸውን ያነበብኩት። ሙሉውን አስነብበኝ ...