የአድዋ ድልና የአሉላ አባ ነጋ ጠላቶች
ከአንተነህ መርዕድ
እነሆ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ኩራት የሆነውን የአድዋን ድል 118ኛ ዓመት ልናከብር ተዘጋጅተናል። ይህንን ታላቅ ቀን ባንድ ትንሽ ማስታወሻ ብዙ ማለት ባይቻልም ለድሉ አስተዋጾ ካደረጉት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አሉላል ላነሳ ፈለግሁ። አሉላ አባ ነጋ ትግራይ ውስጥ በተንቤን አውራጃ መናዌ በምትባል መንደር እንግዳ ቁቤ ከተባሉ ገበሬ ነው የተወለዱት።
በወጣትነታቸው በሚያሳዩት ጀግንነት የአጼ ዮሃንስን የዚያንጊዜውን ካሳ ምርጫን ትኩረት ስበው ነበር።አሉላ በቅድሚያ ጀግነታቸውን ያስመሰከሩት ጉንደትና ጉራዕ በዋለው ጦርነት ለወረራ የመጡትን ግብጾች ለነጋሪም እንዳይተርፉ በጨረሷቸው ወቅት ነው። ከዚህም ድል በሁዋላ በ35 ዓመታቸው ራስ ሆነው ተሾሙ። የመረብ ምላሽ ገዥም ሆኑ።የአስመራን ከተማም ቆረቆሯት። ቁልቁል ወደ ቀይ ባህር እየተመለከቱም ኢትዮጵያን ለመውረር ለሚመጣ ጠላት ሁሉ መቅሰፍት ሆኑት። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)



