ቃል (ፊልጶስ)

ቃል

ፊልጶስ - ከሆላንድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ቃልና የቃል ምሥጢር

ይከብዳል አሉ ከሰማይ ከምድር፤

በቃል ነውና “ይሁን!” ተብሎ የሆነ

ሁሉም ፍጡር፣ ሁሉም ነገር የታመነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍቅር ንጉሥ (አስፋወሰን ዓለምሰገድ)

የፍቅር ንጉሥ

(የኀዘን እንጉርጉሮ)

በአስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ልክ እንደ ነገሥታት፣ ሠራዊት ባይኖርህ

በአንደበትህ ለዛ፣ በሚስበው ድምፅህ

ህዝብህን በፍቅር፣ በውዴታ ገዝተህ

አወይ የአንተ ነገር፣ በድንገት ተለየህ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሥራት አትረሳም (አስፋወሰን ዓለምሰገድ)

አሥራት አትረሳም

አስፋወሰን ዓለምሰገድ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ፕሮፌሠር አስራት ሞተ ብለው

አረዱኝ ከእንቅልፌ ቀስቅሰው።

መቼ አሥራት እንደሰው ይሞታል

ከኢትዮጵያ ጋር ለዘለዓለም ይኖራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሽጉጤ ደሜ - የደም ድምፅ (በልጅግ ዓሊ)

በልጅግ ዓሊ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የዛሬውን አያድርገውና አዲስ አበባ ትንሽ ከተማ ነበረች። አሁንማ በጣም ሰፍታለች። የህዝቡም ቁጥር ጨምሯል። የሽጉጤ ደሜ ታሪክ ሲፈፀም አሁን ካላት ስፋት ጋር ሲወዳደር የትየለሌ ነው። ከሦስት አስር ዓመታት በፊት አንዱ ሠፈር የተፈፀመው ሌላው ሠፈር ይሰማ ነበር። ዛሬማ ምኑ ቅጡ ብሽቅጥቅጡ እንኳን ሌላ ሠፈር የተሠራው የጎረቤትም መርዶ አይሰማም። አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት ሠፈሮች አንዱ ”ልደታ” ነው። ሠፈሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ጥቅጥቅ ብለው የሚኖሩበት ነው። የሠፈሩ ነዋሪ ችግረኝነቱ ሳይበግረው ተፋቅሮ የሚኖር ሲሆን፣ በደስታም ይሁን በኀዘን የማይለያይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትናንት እና ዛሬ (ከሀገረ ኢትዮጵያ)

ከሀገረ ኢትዮጵያ

ወጨጫ ማርያም ሲነግስ በየዓመቱ ከጎረቤቶቼ ጋር እንሄዳለን። ቤተሰቦቼም የሚኖሩት እዚያው አካባቢ ስለሆነ ወጨጫ ማርያምን ካነገስን በኋላ እነሱ ዘንድ እንገባና በሚገባ ተጋብዘን እንወጣለን። በየዓመቱ ስለማንቀር በደንብ ተዘጋጅተው ይጠብቁናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...