ትውስታ ለሙዚቃው ቀማሪ (ጌታቸው አበራ)

ጌታቸው አበራ (መጋቢት ፮ ቀን ፪ ሺህ ፪ ዓ.ም./ማርች 2010)

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በእሁድ ዕለት ዜናው፣ የእውቁን የሙዚቃ ደራሲና ቀማሪ፣ የኮ/ል ሣህሌ ደጋጎን ዜና እረፍት ሲያሰማን፣ አዘንኩኝ። በትዝታ ወደኋላ በመመለስም የልጅነት ጊዜዬን ማሰላሰል ያዝኩኝ። የሙዚቃ በረከት እየመገቡ ላሳደጉን ለኒያ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ያለኝን ከበሬታ ለመግለጽም ይህቺን አጭር ማስታወሻ ለማስተላለፍ ወደድኩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሣህሌ ደጋጎ (ክንፈ ሚካኤል)

Sahele Degagoሣህሌ ደጋጎ

ክንፈ ሚካኤል

ዋ ሣህሌ ታላቁ

ጎምቱ የሙዚቃ ሊቁ

አንተም ጨከንክ እንደ ጓገኛህ

በሕይወት እንደ ነበርከው በእልፊትም ተጎዳኘህ።

ተከተልከው ጥላሁንን

አንድ ላይ ነበርክ ምንም ቢሆን።

ክዘ ሲጀምር ዘመናዊ

አንተ ነበርክ መርአዊ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊቷ አሪታ ፍራንክሊን (ዘነበ በቀለ)

ዘነበ በቀለ

ርዕሱ ብዙዎችን ያሳስታል ብዬ አልገምትም። የሁለቱንም ዘፋኞች ሙዚቃ አገናዝቦ መረዳት የሚቻል ነውና። አሪታ በልጅነት ዘመኗ ”ሬሰኩዩሚ” እያለች ያቀነቀነችው ሙዚቃ በአንድ በኩል የሙዚቃው ርዕስ ጭንቀቷን ገላጭ ቢመስልም፤ በሌላ በኩል ደግሞ የድምፅዋን ልክ ያሳየችበት ዕፁብ ድንቅ የሆነ ዜማዋ ነው። ኢትዮጵያዊቷ አሪታ ፍራንከሊን ደግሞ በባህላዊ መንገድ ችግርን አምቆ መያዝ እንጂ ለአደባባይ አስጥቶ ማሳየት የተለመደ አይደለምና ሁሉን ቻይ ሆና መከራዋን የምትገፋው ድምፃዊቷ ማሪቱ ለገሠ ነች። ሙሉውን አስነብበኝ ...