ተ - ውሽ ሠለሞን ተካልኝ (ግርማዊ ተፈሪ)

Solomon Tekalegne ሠለሞን ተካልኝ ግርማዊ ተፈሪ

ዱሮ ገና ሠለሞን ተካልኝ ያቀነቅናቸውን የነበሩ የነፃነት ዜማዎች ደጋግሜ ስስማ፤ ይህ ሰው ቢያንስ በርታ ሊባል ይገባል በሚል የህዝብ ልጅ ነው ብዬ በግጥም አሞግሼው ነበር። ከዚያ ገልበጥ ብሎ ወደ አዲስ አበባ በመብረር የቆጥ የባጡን ሲዘላብድ ስሰማው፤ አይ ሰው መሆን ምነው ሰውየው እንዲህ ተጃጃለ ድሮስ ከሞኝ ምን ይጠበቃል እያልኩ አላግጨ ዝም አልኩ። ሰሞኑን ደግሞ ‘አወጣሁ’ ያለው ዘፈን አይሉት ምን ስሰማው፤ አይ ይህ ሰው ጃዝ ብለውታልና ዋ ካልተባለ የበለጠ ሊሸናብን ነው አልኩና እነሆ ይችን ወረቀት ጫርኩ። ዘፋኝ ነውና በግጥም ብፅፍለት ዘፈን እንዳይመስለው እነሆ ተ - ውሽ ሠለሞን ብየ በስድ ንባብ ልሰደድበት ጀመርኩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሠሎሞን ተካልኝ - ኢትዮጵያዊው ኦባማ ገርል

አሪስ ታታሊስ

ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሁላችንም የቅርብ ትዝታ ነው። የፓርቲ ዕጩነቱን ከማሸነፍ አንስቶ እስከ መጨረሻው የኖቬምበር 4 ምርጫ ድረስ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ የነበረ ምርጫ ነበር። ታዲያ በዚህ ምርጫ ወቅት ነበር አንዲት ኮረዳ ጎልታ የወጣችው። ስሟ አምበር ሊ ይባላል፤ አሁን ሁሉም በቅጽል ስሟ ”ኦባማ ገርል” እያለ ይጠራታል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሞት ዕኩልነት (ዳግማዊ ዳዊት)

የሞት ዕኩልነት

ዳግማዊ ዳዊት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

እግዜር በፈጠረው - ሰማይና ምድር

ተራራ ሸንተረር - ውቅያኖስ ባህር

ያገባኛል ብሎ - ሰው ባለቤት ሆኖ - ድንበር አበጅቶ

የከርሰ-ምድር ሀብት - በስፋት አካብቶ

አንተ ከዚያ ወዲህ - አንች ከዚህ ወዲያ - ብሎ ተከፋፍሎ

አንዱን እጅግ ደልቶት - ሌላው ተበድሎ

ይኖራል ይሞታል - የመኖር-ሕግ ሆኖ። ሙሉውን አስነብበኝ ...