ምንም ነገር ሳልይዝ ባዶዬን መጥቼ
እውቀት በመሰለኝ ክፋት ተሞልቼ
ግዜዬን ስጨርስ ከዝች ዓለም ስሄድ
ማምለጫዬን እንጃ ከሚጠብቀኝ ፍርድ ሙሉውን አስነብበኝ ...
ተጨነቅ ያለው ሰው አዕምሮው አይረፍ
ያሻው የወደደው ሞልቶ ቢትረፈረፍ
የነገውን ስቦ ያምናውን ጎትቶ
ሲፈጭ ነው የሚኖር ሳይጋግር አቡክቶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...አላህ ቢሻ ኖሮ ብዙ እንድንናገር
አፍን ሁለት አድርጎ በፈጠረ ነበር
ሆኖም በመውደዱ ብዙ እንዳናወራ
አፍን አንድ አደርጎ ሁለት ጆሮ ሠራ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ህይወት አስተምሮት ካልመለሰው በቀር
አድናለሁ ብለህ ይሄን ሰው በምክር
ያለህን አሟጠህ ጆሮው ብትገለብጥ
እመነኝ ጨርሶ አትችልም መለወጥ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...