አጫጭር የሀገር ቤት ምናብ-አከል ዜናዎች
ይነጋል በላቸው
-
ወያኔ ተለጣፊን በማፍራት የሚስተካከለው እንደሌለ አንድ ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኝ ገለጹ
አዲሱ ሹመት የጭቡ መሆኑን ዜጎች ገለጹ
“የሰሞኑ የወያኔዎች የቁጭ በሉ ሹመት የልጅነት ጊዜ የዕቃ ዕቃ ጨዋታን ያስታውሰኛል። እልም ያለ ዐይን ያወጣ የጭቡ ሥራ ነው። ማንን ሊያታልሉ ይሆን እንዲህ እንሻቸው የሚጥሱትን የራሳቸውን ሕገ-መንግሥት ተብዬ ሳይቀር ሽረው ይህን የመሰለ ከማሳቅ ባለፈ የማንንም ቀልብ የማይስብ የአራድነት አይሉት የቂልነት ሥራ የሚሠሩት?” በማለት የገለጡት አንድ የመንደር አዛውንት፤ እንደዚህ ዓይነት ለአንዲት ድሃ ሀገር ለታይታዊው የማስመሰል ቲያትር ሲባል ብቻ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን በመደርደር የብሔሮችን የሥልጣን እኩልነት ለማሳየት መሞከራቸው ሕዝቡን የመሳደብ በንቀት ልምጭም የመማታት ያህል እንደሆነ ገልጸዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
(ምናባዊ)
ተስፋዬ ገብረአብ


