በሜልቦርን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት ተቃወሙ
Ethiopians protested in Meelbourne. በሜልበርን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. (April 24, 2015) የሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ እና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሕብረት ባስተባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ቁጣውን በመረረና እልህና ቁጭት በተንጸባረቀበት መልክ ሲገልጽ አርፍዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስቶክሆልም የመድኃኒዓለም ቤ/ክ በሊቢያ ለተገደሉ ወገኖቻችን ጸሎት ምሕላ ተደረገ

Abune Elias. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. April 22, 2015)፡- ዛሬ ማምሻውን ከ12 ሰዓት (18፡00) ጀምሮ ለሁለት ሰዓታት በስቶክሆልም በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በሊቢያ ለተገደሉት ወገኖቻችን በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የምስራቅ አፍሪካና የአውሮጳ ሊቀጳጳስ የተመራ ሥርዓተ ጸሎት ተደረገ። በርካቶች ሲያለቅሱ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አይሲስ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመው ግድያ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ

በአዲስ አበባ ኀዘኑን ለመግለጽ የወጣው ህዝብ ድብደባ ደረሰበት

ISIS massacre on Ethiopian Christians in Libya

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. April 21, 2015)፡- ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ የሚኖሩ 30 ኢትዮጵያውያንን በጥይት በመደብደብ እና በካራ በማረድ አይሲስ (ISIS) የተባለው አሸባሪ ቡድን በፈፀመው ግድያ በሀገር ቤትና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከፍተኛ ኀዘን ላይ ወድቀዋል። ይህንን ግድያ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ዘግይቶ የኀዘን መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ በመግለጫውም በመላው ሀገሪቱ ለሦስት ቀናት ብሔራዊ ኀዘን ሆኖ እንዲቆይ እንዲሁም በኢትዮጵያና በኤምባሲዎች ጭምር የሚገኙ ባንዲራዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ አዟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር ራሱን አስተዋወቀ

Semayawi Party in Stockholm, Sweden. በስዊድን የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር ራሱን አስተዋወቀEthiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. April 7, 2015)፡- ቅዳሜ አፕሪል 4 ቀን 2015 ዓ.ም. (መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.) የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር በስዊድን ተመስርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመግለጽ፤ የድጋፍ ማኅበሩ ራሱን አስተዋውቋል። በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ዓላማና ተግባርን ጥሪ ለተደረገላቸው ተሰብሳቢዎች ያስረዱት አቶ ሰለሞን ጌታነህ የድጋፍ ማኅበሩ ሰብሳቢ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው አደጋ ላይ ነው

62 ሕፃናት ተገድለዋል
People gather at the site of an air strike at a residential area near Sanaa (Reuters)

Ethiopia Zare (ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ April 2, 20015)፡- የየመን ሑቲ ሚሊሽያ አማጽያንን ለማጥቃት በሳውዲ ዐረቢያ መሪነት በየመን ላይ እየተወሰደ ያለው የአየር ድብደባ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ታወቀ። ለሣምንት በዘለቀው የአየር ጥቃት 62 ሕፃናት መገደላቸውን ዩኒሲኤፍ ገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእነብርሃኑ፣ ፍቅረማርምና እየሩሳሌም የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

ኤልያስ ገብሩ

ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል
‹‹ተጨማሪ ምርመራ ይቀረኛል›› መርማሪ ፖሊስ
‹‹መረጃዎች ካሉ ክስ ይመስረትብን ካልሆነ ከእስር እንለቀቅ›› ተጠርጣሪዎች

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረማሪያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ፍርድ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት ህወሓትን ከዱ

W/o Abeba Gebrehiwot. ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት Ethiopia Zare (ሐሙስ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. March 26, 2015)፡- የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት፣ ኢህአዴግን መክዳታቸው ተሰማ። ወ/ሮ አበባ ኢህአዴግን የከዱት በቅርቡ ለስብሰባ በሄዱባት ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መሆኑ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ግሰለቦች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

ኤሊያስ ገብሩ

‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም። ኢህአዴግ አሸባሪ ነው። ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ

‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው

‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው። እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ

‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ

‹‹ኃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ

ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት እና በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ያሉ 10 ሰዎች ቀርበው ነበር። መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመቀበል እና ከ1-5ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተከሳሾች በእስር ቤቱ ደረሰብን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተያየት ካላቸው ለመቀበል መሆኑን የችሎቱ የግራ ዳኛ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከአአ ዩኒቨርሲቲ ተባረሩ

"አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ!" ዶ/ር ዳኛቸው
Dr. Dagnachew Assefa. ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. March 17, 2015)፡- በውጪ አገር ለሠላሳ ዓመታት የቆዩትና ለሰባት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት የሰሩት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከስራ መባረራቸውን ገለጹ። ዶ/ር ዳኛቸው፣ ኢትዮጵያዊ ማለት መብቱ የሚረገጥ ማለት በመሆኑ፣ አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ በማለት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ