መላኩ ፈንታ

የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ

1.7 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 18, 2021)፦ ከታክስ ማጭበርበር እና ስወራ ጋር በተያያዘ ሊመዘበር የነበረ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የአገር ሀብት መታደግ መቻሉን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፤ በታክስ ማጭበርበር እና ስወራ ሊመዘበር ነበር ያለውን ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ መታደግ የተቻለው ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ ነው።

የኮምሽኑ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከጉምሩክ እና ግብር (ታክስ) ማጭበርበር ወይም ስወራ ወንጀል ላይ በተደረገ ምርመራ ይህንን ያህል የሚገመት የአገር ሀብት ከምዝበራ ከማዳኑም ሌላ፤ ባለፉት ስምንት ወሮች ብቻ ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንም ገልጸዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ እንዳመለከቱት፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ