”የኔ አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ከሚታገሉ ኃይሎች ጋር ነው” አና ጐሜዝ
'ለተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ የማቀርበው ነገር፤ ህዝቡ በምርጫ እንዳይሳተፍ የሚከለክል መልዕክት ማስተላለፍ አይገባቸውም'
በአውሮፓ ፓርላማ የሶሻሊስት ፓርቲ አባልና በኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ተካኺዶ በነበረው ምርጫ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ልዑካን ሊቀመንበር የነበሩት አና ጐሜዝ በቅርቡ ከዩሮ ጋዜጣ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ሁኔታ፣ ስለኦነግ (ስለየኦሮሞ ነፃነት ግንባር)፣ በቀጠናው ስላለው መረጋጋትና ”የቅርብ ወዳጃቸው ናቸው” ተብለው ስለሚጠቀሱት በዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ስለተቋቋመው የግንቦት 7 ንቅናቄ ዙሪያ ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ለኢትዮጵያውያን አንባብያን በሚመች መልኩ በአማርኛ ቋንቋ ተርጉመን አቅርበነዋል።



“ፓርላማ የሚገኙት አባላቶቻችን በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሥራ ሊሠሩ በሚችሉበት ሁኔታ ጥረት ማድረግ አለባቸው” ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ
ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም የሰባዊ መብት ታጋይ በመሆን ለረጅም ዓመታት የኢሰመጉ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። ከዛም ቅንጅትን ትተው እስከወጡበት ጊዜ ድረስ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ቆይተው የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ናቸው። ፕሮፌሠር መስፍን ከፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት ጣሴ ጋር በመሆን በአሜሪካን ሀገር በዘጠኝ ስቴቶች ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቆይተው ባለፈው ሣምንት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። ፕሮፌሠር መስፍን የትጥቅ ትግልን አጠንክረው ሲቃወሙ ይደመጣሉ። ጽዮን ግርማ (የእንቢልታ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ) ስለትጥቅና ሠላማዊ ትግል ስልት ከፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም ጋር ቆይታ አድርጋለች።
የታይም መጽሔት ዘጋቢ በአዲስ አበባ ተገኝቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ስለ ወቅታዊ የረሃብና እርዳታ ጉዳዮች ያደረገውን ቃለምልልስ ሙሉ ቃል በዛሬው ዕለት (እሁድ ነኀሴ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. / August 10, 2008) የተነበበውና ሀገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ በአማርኛ ተርጉሞ እንደሚከተለው አቅርቦታል። 


