የደራሲው ማስታወሻ - የመጽሐፍ አቃቂር
ተስፋዬ ዮሐንስ
... ተስፋዬ ‘የባርነት’ ዘመኑን በመቃኘት ያሳለፈውን ህይወት፣ ገጠመኙን፣ የታዘባቸውን፣ ወዘተ፣ በጭልፋ እየቆነጠረ ያቋድስ ጀመር። ‘የጋዜጠኛው ማስታወሻ’ የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ለንባብ አበቃ። ብዙዎች አበጀህ፣ ደግ አደረግ አሉት። ቀጣፊ ያሉትም ነበሩ። ኤርትራዊ የዘር ሃረጉን በመቁጠር የሻዕቢያ ደጋፊ ያሉትም አልጠፉም። በተለይ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና አባላት፣ ገበና አጋለጠ በማለት ብዙ ጽፈውበታል። ሙሉ በሙሉ ከባርነት በወጣበት ‘የጋዜጠኛው ማስታወሻ’ መጽሐፉ ላይ የብዙ ሰዎች ስሞች ተነስቶ ተስፋዬ ከበድ ከበድ ያሉ ክሶችና ውንጀላዎች ደረድሮአል። አንዳቸውም አላስተባበሉም። ለምን? ... ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ ተስፋዬ ሌላ መጽሐፍ ደርሶ ለንባብ አብቅቷል፤ ‘የደራሲው ማስታወሻ’። መጽሐፉ 25 ራሳቸውን የቻሉ ክፍሎች አሉት። ይህ አቃቂር በሦስት ዐብይት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። 1/ መጽሐፉን መድረስ ለምን አስፈለገ? 2/ መጽሐፉ ያቀፋቸው ዋና ዋና ጭብጦች ምንድናቸው? 3/ የመጽሐፉ ደካማ ጎኖችስ? ... ሙሉውን አስነብበኝ ...





