ኢሕአፓ እና ታሪኩ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ከኢያሱ ዓለማየሁ

ነገርን ነገር ያመጣዋል እንዲሉ በቅርቡ አንዲት የተበሳጨች ኢትዮጵያዊ- የኢሕአፓ ታሪክ እያሉ መጽሃፍ ጻፍን በሚሉ ዋሾዎች በመናደድ--በስም ጠቅሳኝ የድርጅቱን ታሪክ ባለመጻፌ ወቅሳኝና ውቀሱት ስትል መልዕክትና ምሬት ፈረንጆቹ ፌስ ቡክ በሚሉት አማካይነት አሰምታለች። ወጣት ናት በሚል ግምት አንቺ ብያለሁና ከተሳሳትኩ ይቅርታ። ብስጭቷ ቢገባኝም ታሪክ መጻፍን በተመለከተ የተንደረደረችበት ግምትና ሌሎችም የሚያሰሙት ትችት በመሰረቱ የተሳሳተ ነው። ላብራራ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተስፋይቱ ምድር የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

መስፍን ማሞ (ሲድኒ-አውስትራሊያ)

ለቀደሙት የተባለውን ሰምታችዃል……… ይህም ተፅፏልና!

ለምትበልጠው ፀጋ ቅኑ። እኔም ዳግመኛ እጅግ የበለጠ ሌላ ጎዳና አሳያችዃለሁ፤ በሰዎች ሁሉ ቋንቋና በመላእክት ቋንቋ ብናገር፤ ትንቢትም ብናገር፤ የተሰወረውን ሁሉና የጥበብን ሥራ ሁሉ ባውቅ፤ ተራራም እስካፈልስ ድረስ ሃይማኖት ቢኖረኝ፤ ያለኝንም ሁሉ ለድሆች ባበላ፤ ዳግመኛም ሥጋዬን ለእሳት ቃጠሎ ብሰጥ፤ ፍቅር ከሌለኝ የተጠቀምሁት የለም። ፍቅር ያለው ሰው ሩህሩህ ትዕግስተኛም ነውና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደስ”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ከጸጋዬ ገብረመድኅን አርአያ

ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እየሳቁ ማልቀስ! (የማለዳ ወግ)

የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar InactiveStar Inactive

ነቢዩ ሲራክ

በለጋ እድሜዋ ትዳር መስርታ ሁለት ትጉህ መንታ ልጆች የታደለች እህት ከትዳር ጓደኛዋ ችግር ገጠማት። የ “ተበዳይ ነኝ!” ባይ ወዳጀን ምሬት ደጋግሜ ብሰማም ከቀናት በፊት “በደለኝ!” ያለችው የትዳር አጋሯ በኮሚኒቲው ሽምግልና ኮሚቴ በኩል ክስ መስራቱን እና የክስ ጥሪ እንደደረሳት ሰማሁ። ከአሰር አመት በፊት እድሜዋ ገና የ17 አመት እያለ የዛሬ የ12 አመት እድሜ የሆነውን ትልቁን ልጀን ያሳደገችውን እህት የቆየ አብሮነት ትውስታ እያሰብኩ የአለመግባባቱን ሽምግልና ወደሚከወንበት የጅዳ ኮሚኒቲ ሽምግልናውን ለመታዘብ መጓዝ ጀመርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ተመስገን ደሳለኝ Temesegen Desalegnተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ) 

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች … ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም። እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ