ይሄይስ ተኣምኖ በእግዚአብሔር (ይሄይስ አዕምሮ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ይሄይስ አዕምሮ

እንደምን ሰነበታችሁልኝ! ባገራችን አንድ አባባል አለ፤ ”ከብቶች እንኳን በየፊናቸው ዱር ውለው ማታ ሲገናኙ ’እምቡዋ’ በመባባል ሠላምታ ይለዋወጣሉ” የሚል። በሌላም በኩል ”እንደከብት ዝም ብለህ አትቀላቀል” የሚለውን ቢፃዊ ግሳጼም ሳንዘነጋ። በ’ርግጥም ነገርን በሠላምታ መጀመር ጥሩ ነው - አሁንም ”ከሺህ ሠላምታ አንድ ሜታ!” ወይም ሦስት ጊዜ ሠላምታ አንዱ ለነገር ነው!” የሚባሉትን ፀረ-ሠላም(ታ) ኃይሎች ማለቴ አባባሎች ሳንረሳ። እናም ሠላምታየ በያላችሁበት ይድረሳችሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀላጤ አርቃቂው ጠ/ሚኒስትር

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በዚች ገጠር ወረዳ ብቸኛ ቀላጤ ጸሀፊ የሆነው "አስናቀ ሽቦ" ሰዎች ሲካሰሱ፣ አቤቱታ ሲያቀርቡ፣ ውል ሲፈራረሙ ረቂቅ አዘጋጅቶ በገጽ አንድ ብር እየተቀበለ ቀላጤ ይቸከችካል። ታዲያ ከዕለታት አንድ ቀን በዚያች የገጠር ከተማ ሁከት ይቀሰቀሳል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

የአቶ መለስ ዜናዊ ደብዳቤ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

PM Meles Zenawiበሸዋይልማ ኪዳኔ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)

Ethiopian Peoples‘ Revolutionary Democratic Front (EPRDF)

ጉዳዩ፦ የወ/ት ብርቱካንን አፈታት አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ

የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ከእስር ቤት በምህረት መለቀቅን አስመልክቶ በቀበሌ፣ በወረዳ እና በዞን ደረጃ በሚገኙ አባላትና ካድሬዎቻችን እንዲሁም በዳያስፖራ በሚገኙ ደጋፊዎቻችን ዘንድ የመንግሥትን እርምጃ በሚገባ አልተረዱም የሚሉ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ስለቀረቡልኝ፤ ይህን ደብዳቤ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርነቴ ሳይሆን እንደ ኢህአዴግ ሊቀመንበርነቴ ለመጻፍ ተገድጃለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብርቱካን መፈታት በእናት አይንና በንስር አይን

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

አለቃ ተክሌ - ከቫንኩቨር-ኦታዋ (ካናዳ)

የ”ሞራል” ብቃትና የሞራል እጥረት ለነገሩ የተፈታው ማነው?

እንዳጋጣሚ ሆኖ ብርቱካንን ለመገምገምና በብርቱካን ላይ የ”ሞራል” ብያኔ ለመስጠት የሚያስችል የ”ሞራል” ብቃት የለኝም። ግን እንደ ባህል ይሄ “አንተ ወይም አንቺ ይሄንን ለማለት ወይም እንዲህ ለመናገር የሞራል ብቃት የለህም/ የለሽም” የሚል መፈክር ደሜን ያፈላዋል። ፖለቲከኞች ላይ የሞራል ፍርድ ለመስጠት የሞራል ብቃት አያስፈልግም። ፖለቲከኞችና ስራቸው እንደ መርህ ለማናቸውም ግምገማና ፍርድ የተጋለጡ ናቸው። ኦባማንና አስተዳደሩን ለመገምገም የአሜሪካ ህዝብ የተለየ የሞራል ብቃት አያስፈልገውም። መንጌ ሃራሬ ቤቱ ቁጭ ብሎ እሱ የሰራውን ቢሆንም እንኩዋን የሚደግመው መለስን መገምገምና ማብጠልጠል ይችላል። ብርቱካንንና ፖለቲካዊ እርምጃዋን ለመገምገም የግድ ለቅጽበትም ቢሆን በቃሊቲ መታሸት የለብንም። በቂ ምክንያት እስካለና በቅን ልቡና እስከተነሳሳን ድረስ የፖለቲካ መሪዎችን መገምገም መብት ነው። እነሆ ከብርቱካን ጉዳይ ጋር በተያያዘ መብቴን ልጠቀም ነው። እንዳጋጣሚ ሆኖ ግን በበጎ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የስደት የፖለቲካ ትግል አጋዥ እንጂ ወሳኝ አይደለም!

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በቃሊቲ እሥር ቤት እያለች መራራ ስቃይ እንደደረሰባት ሳትደብቅ ደጋግማ ገልጻለች። የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጠኛ፣ አብይ ተክለማሪያም፣ የናዚ ጀርመንን ታሪክ በማስታወስ “Verschärfte Vernehmung” (silent Torture) በማለት ለማስረዳት እንደሞከረው፣ አሰቃቂ የስነ ልቦና ቶርቸር እንደተፈጸመባት የሚያከራክርና የሚያወዛግብ አደለም።1

ሙሉውን አስነብበኝ ...

... ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ስምንት - አያልሰው ደሴ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ስምንት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በውሳኔው መሠረት ጉባዔ አዘጋጁ ክፍል ስለዚህ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ዓላማና አስፈላጊነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ቅስቀሳዎችና ገለፃዎችን አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...