ኢትዮጵያ፡ ሕዝባዊ ተቃውሞና የወታደራዊ መንግሥት ጥያቄ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

እስክንድር ነጋ

የደርባባውና የ82 ዓመቱ አዛውንት ሆስኒ ሙባረክ ከስልጣን መውረድ ዓርብ አመሻሽ ላይ ሲበሰር፣ በግብፅ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ እልልታና ሆታ ቀለጠ... ሕዝብ በደስታ ሰክሮ ሌሊቱን አሳለፈ.... አይ ካይሮ ያቺን ምሽት!... እንዴት ትረሳለች?... እኛስ አብረናቸው አላደርንም እንዴ?... ዕድሜ ለአልጀዚራ፣ ለቢ.ቢ.ሲ፣ ለሲ.ኤን.ኤን፣ ለፕሬስ ቲቪ... የካይሮ ሕፃናት እንዴት ይረሱናል?... ገብቷቸው ይሆን እንዲያ የፈነጠዙት?... ጨለማውን ብርሃን እንደዋጠው እውን ለእነሱም ታይቷቸው ነበርን?... ቀልባቸው ነግሯቸው ይሆን?... የትላልቆቹማ ምኑ ይወራል... በእነሱ ደስታ እኛም እምባ ተራጭተናል ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአምባገነኖች የመጨረሻ ቀናትና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁዩኔታ! (አንዷለም አራጌ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ምዕራቡ ዓለም በዋናነነት በሁለት ዋና ምሰሶዎች ላይ የተመረኮዙ መርሆዎችን በማራመድ ከኮሚኒዝም ጋር የተያያዘውን ትንቅንቅ በድል ለማጠናቀቅ ትልሙን ጣለ። ሁሉን አቀፍ ፀረ-ኮሚኒዝም ጦር መስበቅ እና የተጠናከረችና የፈረጠመች እስራኤልን በመኮከለኛው መስራቅ ማደላደል። እነዚህ ሁለት ምሰሶዎች ላይ በመመርኮዝ ኮሚኒዝምን የሚያወግዙና የእስራኤልን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥሉ አምባገነኖች ሁሉ በዓለም ዙሪያ በሕዝባቸው ላይ ለሚያደርሱት ምሬትና ዋይታ ኬላው ከፍ ብሉ ተነሳላቸው። በኋላ ላይ በፀረ-ሽብር ዘመቻው ተባባሪ ለሆኑ አምባገነኖችም ይኸው ቡራኬ ተቸራቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክቡር ሚኒስትር (ከሪፖርተር ጋዜጣ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

[በሥራ ምክንያት ውጭ አገር በሔዱ ቁጥር ክቡር ሚኒስትሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ገብተው በእውቀታቸውና በገንዘባቸው እንዲሠሩና የልማት አጋር እንዲሆኑ ይወተውታሉ። አንድ የዲያስፖራ አባልም ይህን መልዕክት ተቀብሎ ከወንድሙ ጋር አንድ ፋብሪካ ለማቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል። ያጋጠመውን ሁሉ በየጊዜው ለክቡር ሚኒስትሩ ይነግራቸዋል]

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኢሕአዴግ መሪዎች (በሊቢያ በኩል የተላከ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

እስክንድር ነጋ - (አዲስ አበባ)

ፓሪስ፤ ቅዳሜ፣ ምሣ ሰዓት፣ መጋቢት 10/2003

የሳርኮዚ የታላቅነት ህልም እየሆነ ነው... ምሳ ግብዣቸው ላይ የዓለም ዋና ዋና መሪዎች በአድናቆት ታድመዋል... «በመሪዎች መሪነት» አድምቀዋቸዋል ... ትንሽ የማይባሉ ፈረንሣዮች እንባ እየተናነቃቸው ነው፤ በታላቁ ንጉሣቸው ሊዊ 16ኛው ዘመን የነበረው ኃያልነታቸውን እየታወሳቸው ... ዛሬ ፈረንሳይ የዓለም መዘውር ሆናለች.... ሳርኮዚም በሊዊ 16ኛው ተመስለዋል። ኦባማ ብቻ የውሃ ሽታ ሆነዋል.... የመሪነቱን አክሊል ለአውሮፓዊያን አቀብለው ወደ ብራዚል ነጉደዋል። ግራ አያጋባም ጃል?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

"መለስና ጉዋደኞቹ ሁለገብ የንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር" በሥሩ ላቋቋማቸው እህት ኩባንያዎች ከ1967ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት ለልዩ ልዩ ክፍት የሥራ መደቦቹ ሥራ ፈላጊዎችን እያወዳደረ ሲቀጥር መቆየቱ ይታወቃል። በ1967 ዓ.ም. በዐዋጅ ቁጥር መዜአ/666/6606/66 ዓ.ም. መሠረት በሰባት አባላትና በሰባት ሶቪየት ሠራሽ አሮጌ ክላሽኖች መነሻ ካፒታል ትግራይ ላይ የተቋቋመው መለስና ጉዋደኞቹ ሁለገብ የንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር በአሁኑ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላትን ያቀፈ ሲሆን ካፒታሉም በብዙ ቢሊዮኖች የሚገመት ዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ የደረሰ መሆኑን በማስታወስ በተለይ ደንበኞቹንና ወዳጆቹን እንኩዋን ይህን ያልታሰበ ድንቅ አጋጣሚ ለመታዘብ በቃችሁ በማለት የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ይገልጻል። በዚህ አጋጣሚ ታሪካዊ ጠላቶቹ እንደተለመደው ሁሉ እርር ድብን እንዲሉ ልባዊ ግብዣውን ሲያስተላልፍላቸው አሁንም በታላቅ አክብሮትና ሥጋዊ ሃሤት በመታጀብ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...