ምነዋ ኢትዮጵያ …?
ፊልጶስ
እንደ ይሁዳ ከዱ፣ ልጆችሽ ሸፈጡ
እንደ ኤሳው ሆኑ፣ ቡክርናቸውን ሸጡ
በመታመን ፋንታ፣ ኑፋቄን መረጡ።
እንደ ባህር አሸዋ - እንደ ሰማይ ከዋከብት
ምነዋ ኢትዮጵያ ... በዛብሽ ጠላት? ...
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፊልጶስ
እንደ ይሁዳ ከዱ፣ ልጆችሽ ሸፈጡ
እንደ ኤሳው ሆኑ፣ ቡክርናቸውን ሸጡ
በመታመን ፋንታ፣ ኑፋቄን መረጡ።
እንደ ባህር አሸዋ - እንደ ሰማይ ከዋከብት
ምነዋ ኢትዮጵያ ... በዛብሽ ጠላት? ...
ሙሉውን አስነብበኝ ...ኃይለጊዮርጊስ ደስታ
ከነገሮች ሁሉ ሚዛን የሚደፉ፤ ሁለት ዓብይ ነገር፣
ወደ ላይ ቢወጡ፤ ወደ ታች ቢወርዱ፣ በዚች ዓለም ምድር፤
ተምሳሌት፣ እኩያ፣ ወደር የሌላቸው፤ እናትና ሃገር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ይነጋል በላቸው
ድሮ የምናውቀው፣ ወጉ የሽምግሌና
በደልን የሚያረክስ፣ የጎበጠውን የሚያቃና
ነበር ብቃት ያለው፣ የሞራል ልዕልና።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ያቶ መለስ ነገር ግራ የሚያጋባ
ሬሳቸው አድዋ ሳጥኑ አዲሳ አባ
ጌታው አቶ መለስ በቁም ሰው የፈሩ
ሞተው ባደባባይ መታየት ጀመሩ
አወይ አቶ መለስ የብልጦቹ ቁንጮ
ቀብራቸው ሆነ አሉ በእንባ መዋጮ
መች በንባ አበቃና የሳቸው ቀብር
መዋጮው ቀጥሏል ከድሃው ቤት ብር
በቁማቸው ሳሉ እድር መግባት ትተው
አወይ ንፉግ ጠባይ ቀባሪ አሳጣቸው
ጌታው አቶ መለስ ለሰሩት ሥራቸው
በላይኛው መንደር የት ይሆን ቤታቸው
አስለቃሿ ስትገጥምና ህዝቡ ሲቀበል እንደዚህ ይመስለኛል ግን እርገጠኛ አይደለሁም፤
(ህዝቡ) ዋይ ዋይ !
(አስለቃሽ) ዋዬ ወየው !
(አስለቃሽ) ያቶ መለስ ነገር ግራ የሚያጋባ
(ህዝቡ) ዋይ ዋይ !
(አስለቃሽ) ዋዬ ወየው !
(አስለቃሽ) ሬሳቸው አድዋ ሳጥኑ አዲሳ አባ
(ህዝቡ) ዋይ ዋይ !
(አስለቃሽ) ዋዬ ወየው !
………………………………………..
…………………………………………….
……………………………………………..
(ህዝቡ) ውይ ! ውይ !ውይ !ውይ ! ውይ !
(አስለቃሽ) እንዲያ !
እርገጠኛ ስላልሆንኩ፤ በእድሜ ጠና ካሉ እህቶቻችን ጠይቀህ አርሙና፤ ከተቻለም ሌሎች ግጥሞችን ጨማምራችሁ፤ እንደገና ጻፉና፤ « አስለቃሹ » በሚል የብእር ስም ከመለስ የቀብር ቀን በፊት በአስቸኳይ በተለያዩ ድረ ገጾች በትኑት ::
እኛ በነጻው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በግድ አልቅሱ ተብለው ለሚጨነቁ ወገኖቻችን መብት ዘብ የመቆም ግዴታ አለብንና አደራ ::