የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፲፯
ድጋሚ ተነስተህ
የወሬ አውሎ ንፋስ ምቶህ ብትቀበር
ሞቻለሁኝ ብለህ ዝም ብለህ አትቅር
ተንኮል ምቀኝነት ክፋት የጋረደህ
እንዳልኾንክ አሳየው ድጋሚ ተነስተህ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የወሬ አውሎ ንፋስ ምቶህ ብትቀበር
ሞቻለሁኝ ብለህ ዝም ብለህ አትቅር
ተንኮል ምቀኝነት ክፋት የጋረደህ
እንዳልኾንክ አሳየው ድጋሚ ተነስተህ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ሞኝ ነህ! እንዳልሽኝ፣ ያኔ! እንደነገርሽኝ፤
በዛው የሞኝ እግር፣ በዛው የጅል ጫማ፤
የብልጦች መሔጃን መንገድ ሳልሻማ፤
እዚህ ደርሻለሁ - ያንቺን ሰማሁልሽ
በብልጦች መንገድ ላይ ደንቃራ እንደረገጥሽ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አላምርበት አለ ይሄ ዘመን ከፋ
ሞት በጅምላ ኾነ ቀረ በወረፋ
እባክህ ፈጣሪ ቀንስ ከሞታችን
ስንያዝ ከንቱ ነን ትንሽ ናት አቅማችን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





መሣሪያ ጨብጦ ተሸክሞ ጥይት
አይተን ምንዋጋው ነበር ድሮ ጠላት
የዘንደሮው ባሰ ያሁን ደመኛችን
ሳናየው እያየ ደርሶ ገዳያችን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





በኑሮው በጤናው ሁሉ ተሟልቶለት
ሲጠላ ለሚኖር ማስመሰል አቅቶት
አስመሳይ የኾነ አስመሳይ ላልኾነው
ሊመክረው ቢነሳ ምንድነው የሚለው?
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የሀብት መለኪያው መስፈሪያው ገረመኝ
ሀብታሙን ድሀ አ'ርጎ ምስኪን ነው የሚለኝ
እሱ ድሀ አይደለም፤ ደሀ ኾኖ አልኖረም አውቃለሁኝ እኔ
በጁ ባይዝ እንኳን፣ ዘርፎ ይሠጥ ነበር እጅግ ብዙ ቅኔ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የትኛው ነው የኛ? የቱ ነው የነሱ?
አብሮ ተቆላልፎ ተጋምዶ እርስ በእርሱ
ኧረ በሕግ አምላክ! የኛ የኛ አትበሉን
የናንተም የኛ ነው፣ የኛም የናንተ ነው፣ ባዕድ አይስማብን!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ሕሊናውን ጋርዶ በሰው የሚነዳ
አይቀርም መክፈሉ ያልበላውን እዳ
ይልቅስ ይሻላል ራስን መዳበስ
እጅን በገዛ እጅ፤ ከንፈርን በምላስ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የሰው ልጅ ተፈጥሮ፣ ጠቅላላ ባሕርይ፣ ስለሚወራረስ፣ አንዱ ከአንዱ ጋራ
በደልን ለማጥፋት፣ ግፍን ለማስቀረት፣ አንተም በዛው መንገድ ሌላ ግፍ አትሥራ።
ሰው መኾን መርሳት ነው፣ ተፈጥሮን መዘንጋት፣ አመልን ማዳፈን
ክፋትን ተንኮልን፣ ሴራ መጎንጎን፣ አንተ እንደማታውቀው እንዴሌለህ መኾን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ሰው ኾነህ ተፈጥረህ ሰው መኾን አትጥላ
እሚያዋጣህ የለም ሰው ከመኾን ሌላ
መነሻ ጥፋቱ ለሰው ሰው ችግሩ
ሰው ሳይኾን ሰው ኾኖ ከሰው ጋር መኖሩ
ሙሉውን አስነብበኝ ...