ዜና - News

የቀድሞ ዬዩኒቲ ኮሌጅ ባለቤት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ

“ነገሮች እዚህ ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ዝም ብለን በመመልከታችን ይቅርታ ልጠይቅ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ፍስሓ እሸቱ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም. March 7, 2012)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባለቤት የነበሩት ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በደል ሲደርስ ዝም ብለው መመልከታቸው አግባብ እንዳልነበረ ገልጸው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ ሜካናይዝድ ኃይል ተሰማራ

ኃይለማርያም ደሳለኝና ኦሞት ኦባንግ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቁ

ሦስት የጥበቃ ኃይሎች ተገድለዋል፣ አንድ ቆስሏል

በጋምቤላ ክልል የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በርካታ ወታደሮችንና ብረት ለበስ የጦር መሳሪያ በማሰማራት አውጫጪኝ እያካሄደ እንደሆነ ተሰማ። የአገዛዙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የክልሉ ፕሬዚዳንት ወደ ደቡብ ሱዳን አመሩ። ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ሲፈጽሙ የኢታንግ ወረዳ መምህራን ስራ ማቆማቸው የክልሉን ውጥረት መባባስ እንደሚያሳይ ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

2ቱ ጀርመናዊያን ታጋቾች ተለቀቁ

"ያቆየኋቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች መንገድ ዘግተውብኝ ነው" - አርዱፍ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም. March 7 , 2012) የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) ላለፉት 7 ሳምንታት ያህል አግቶ ያቆያቸውን ሁለት ጀርመናዊያን ጎብኚዎች ለአካባቢው ሽማግሌዎችና በኢትዮጲያ ለጀርመን ኤምባሲ ተወካዮች አሳልፎ እንደሰጠ ትላንት ማክሰኞ የካቲት 27 ቀን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” አሉ (በመምህሩ መልካሙ)

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ የክልሉ ፓርቲ ባደረገው ድርጅታዊ ግምገማ ውሳኔ አስተላለፈ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከአዲስ አበባ የመጡት የኦርቶዶክስ አባቶች የሽምግልና ቃላቸውን ማፍረሳቸው ተገለጸ

“የሽምግልና ጉባኤው ላደረገው ጥረት ሊመሰገን ይገባል” ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መልከ ጸዲቅ

“ቤተ ክርስቲያኗ ለ4 ተከፍላለች” ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ

“በህገ መንፈሳዊ መሰረት በፓትርያርክ ላይ ሌላ አይሾምም ከተሾመም ለመጀመሪያው ይጸናል” መላከገነት ገዛኸኝ

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ.ም. February 26, 2012)፦ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስና በአዲስ አበባ ተቀማጭነቱን ያደረገው በአቡነ ጳውሎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ መሀከል ከሳምንት በላይ የፈጀው በአሜሪካዋ ግዛት አሪዞና ድርድር ለለቀጣይ ውይይት ለሀምሌ የተቀጠረ ቢሆንም የአዲስ አበባ ተደራዳሪዎች የሽምግልና ቃላቸውን ማፍረሳቸው ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የየመኑ አብደላ ሳላህ ወደ አዲስ አበባ ሸሽተዋል ተባለ

“ወደ የመን የሚመለሱ አይመስለኝም” ዲና ሙፍቲ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም. February 25, 2012)፦ በህዝባዊ የተቃውሞ ማእበል ከስልጣናቸው የተወገዱት የየመኑ ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ወደ የመን ተመልሰው እንደማይሄዱም እየተገለጸ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስብሃት ገ/እግዚአብሔር በመጨረሻዋ ሰዓት

Sebhat Gebregziabher ስብሃት ገ/እግዚአብሔር

“በሰላም ነው ማረፍ የምፈልገው ከዚህ በሗላ መኖር አያሻኝም።” ጋሼ ስብሃት

“አካሉ ቢደክምም አእምሮው ግን አስከመጨረሻው የሰላ ነበር” ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ

 

Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. February 21, 2012)፦ በስነ ጽሁፍ ስራዎቹ ከፍተኛ ዝናንና ክብርን ያተረፈው አንጋፋው የስነ ጽሁፍ ሰው ደራሲና ጋዜጠኛ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ባደረበት የጉሮሮ ካንሰር ህመም ምክንያት ሰኞ የካቲት 12 ቀን ከሌሊቱ 9ሰዓት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኦታዋ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩ አርበኞች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

ፎረም ኦታዋ ለሰብዓዊ መብትና ለዲሞክራሲ በሚል መጠሪያ የተሰባሰቡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ እስር ቤት ተጥለው በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ አርበኞችና ቤተሰቦቻቸው መርጃ የሚሆን ገንዘብ አሰባስበው ወደ አገር ቤት ላኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የአረብ ቲቪዎችን እያወከ ነው

በኢሳት የተጀመረው እወካ ለአረብ ሀገራት ተርፏል

የእውቀት ማነስ ነው ተብሏል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 10 ቀን 2004 ዓ.ም. February 18, 2012)፦ የኢትዮጵያ መንግስት የተቃዋሚዎችን ድምጽ ለመገደብ የተያያዘው የጃሚንግ (የእወካ) ስራ በርካታ የአረብ ቴሌቭዥን ጣቢያዎችንም ከስርጭት ውጭ እያደረጋቸው መሆኑ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኦሞ ሸለቆ የ200ሺህ ዜጎች ህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል!

“አንፈናቀልም” ያሉ እየታሰሩ ነው

Ethiopia Zare ( ሐሙስ የካቲት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. February 15, 2012)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ በመባል የሚታወቀው አካባቢ መንግስት በህንድ ኩባንያዎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለሚታገዘው ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮግራም እንዲውል 300ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በመመደቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ህልውና አደጋ ውስጥ ወደወቋል ሲል አልጀዚራ ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

Template by A4