ዜና - News

የኢትዮጵያ ጦር በሱማሊያ ዳግም የመብት እረገጣ እያካሄደ ነው

. አካለ ስንኩል ሳይቀር ተደብድበዋል

. ጭካኔው ከአልሸባብ የከፋ ነው ተባለ

(ልዩ ዘገባ - ኢትዮጵያ ዛሬ)

Ethiopia Zare (እሁድ መጋቢት 24 ቀን 2004 ዓ.ም. April 1, 2012)፦ በድጋሚ ወደ ሱማሊያ የዘመተው የኢትዮጵያ ሰራዊት የሱማሊያ የሽግግር መንግስትን ከመደገፍ ሚሊሻዎች ጋር በመሆን ከአልሸባብ ባስለቀቃቸው የሀገሪቱ ከተሞች ውስጥ ሰፊ የመብት ረገጣ እየፈጸመ መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው መግለጫ ላይ አመለከተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእርሻ መሬቶችን በሊዝ የመቸብቸቡ ሂደት እንደ አዲስ ሊፋጠን ነው

Ethiopia Zare  ማክሰኞ መጋቢት 19ቀን 2004 ዓ.ም. March 27, 2012)፦ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ የእርሻ መሬቶችን ለባለ ሀብቶች በሊዝ የመሸጡን ሂደት አቋርጣለሁ ባለ በሳምንቱ የፈጠነ ሽያጭ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዋልድባ ገዳምን መታረስ በመቃወም 1ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ ሰልፍ ወጡ

ጥሪው ለህጋዊው ሲኖዶስ፣ ለገለልተኞችም ሆነ ለአባ ጳውሎሰ ተከታዮች ተላልፏል

የተገኙት የህጋዊው ሲኖዶስ አባቶች ብቻ ነበሩ

(የተቃውሞ ሰልፉን ቪድዮ ለመመልከት ይህንን  ይጫኑ )

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2004 ዓ.ም. March 26, 2012)፦ ዋልድባ በመባል የሚታወቀውንና ለዘመናት  የመነኮሳት መመነኛ በመሆኑ ከታሪካዊዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማት በዋናነት ተጠቃሽ የሆነው ገዳም የስኳር ፋብሪካ ለመስራት በሚል ሰበብ የተያዘውን የእርሻ ቁፋሮ በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አል-አሙዲ 4ቢሊየን ዶላር እንዲያገኙ ደሀው ህዝብ ሊፈናቀል ነው

ተፈናቃዮች ካሳ አይሰጣቸውም

የአካባቢ ብክለት ስጋት ፈጥሯል

(ልዩ ሪፖርታዥ-ኢትዮጵያ ዛሬ)

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. March 24, 2012)፦ ንብረትነቱ የሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ የሆነው ብሔራዊ የማዕድን ኮርፖሬሽን (NMC) በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ያገኘውን መጠኑ 550 ሺህ ኪሎ ግራም የተገመተ የወርቅ ክምችት ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆኑ ሲታወቅ ከዚሁ ጋር በተገናኘ የአካባቢው ነዋሪዎች ያለ አንዳች የካሳ ክፍያ በግዳጅ ሊፈናቀሉ እንደሆነ ተገለጸ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ወታደሮች በባድሜ በኩል ድጋሚ ጥቃት ሰነዘሩ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2004 ዓ.ም. March 17, 2012) የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ድንበሬን ጥሳ ለፈጸመችበት ጥቃት ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድባት ይገባል በማለት ለጸጥታው ምክር ቤት ክስ ባቀረበች በማግስቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዛሬ አዲስ ጥቃት መሰንዘራቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ኢትዮጵያችን ሁሉም አይነት ሴቶች ያስፈልጓታል” አቶ ኦባንግ ሜቶ

Obang Metho አቶ ኦባንግ ሜቶ Ethiopia Zare (መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. March 16, 2012)፦ የአገራችን ግማሽ ህዝብ የሚሆኑትን ሴት እህቶቻችን ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬቱ ያማረ እንደማይሆን፣ ቢሆንም ራሱን ለጥፋት እንደሚያጋልጥ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤይሩት ስቃይ የደረሰባት ወጣት ኢትዮጵያዊት ሞተች

አንዳንዶች ”ራሷን አጠፋች” የተባለው ለሽፋን ነው ይላሉ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንጽላ ፊት ለፊት በሊባኖሳውያኑ ዓሊ ማህፉዝና ግብረአበሮቹ ፀጉሯንና ክንዷን በመጎተት እያሰቃዩ በመኪና አፍነው የወሰዷት የ33 ዓመትዋ ወጣት ዓለም ደቻሳ ዛሬ ጠዋት ራስዋን እንዳጠፋች ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤይሩት ጎዳና በኢትዮጵያዊቷ ላይ የተፈጸመው ግፍ ክፉኛ ቁጣ አስነስቷል

Ali Mahfouz ወጣት ዓለም ደቻሳን አሰቃይቶና አንገላቶ በመኪና ያፈናት ዓሊ ማህፉዝ“አጥቂው ላይ ተገቢ ርምጃ እንዲወሰድበት ወስነናል” የሊባኖ የሥራ ሚኒስትር

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ በሊባኖስ መዲና ቤይሩት ውስጥ ካለው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በአንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ ድብደባና እንግልት ሲፈጽምባት የሚያሳይ ፊልም ከተሰራጨ ወዲህ በአለም ዙሪያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ክፉኛ ቁጣ እንዳስነሳ የተለያዩ አለም አቀፍ የዜና አውታራት ዘገቡ።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጋምቤላ ሃያ ወንድ የኮሌጅ ተማሪዎች በጥይት ተገደሉ

አምስቱ ክፉኛ ቆስለዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ ከትናንት በስቲያ ሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ከጎደሬ ወደ ጋምቤላ በሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍው የነበሩ 25 ወንዶች ተማሪዎችና ወጣቶች ካርሚ በምትባል ስፍራ ላይ በጥይት ተደብድበው 20ዎቹ ሲሞቱ 5ቱ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጨካኙና የአረመኔው ጆሴፍ ኮኒ አደን ኢንተርኔትን አጨናነቀ

ጆሴፍ ኮኒ በኡጋንዳ ከ60 ሺህ በላይ ሕፃናትን ጠልፏል

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. March 9, 2012)፦ የኡጋንዳው የጎሬላ ተዋጊዎችና "የጌታ ተጋዳይ ሠራዊት" (Lord’s Resistance Army - LRA) መሪ የሆነውን ጨካኙንና አረመኔውን ጆሴፍ ኮኒን ለማደን በኢንተርኔት የተሰራጨው የ30 ደቂቃ ቪዲዮ በአራት ቀን ውስጥ በዩቲዩብ ብቻ ወደ 60 ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘቱ ታወቀ። የቪዲዮው ዓላማ ጨካኙን በዓለም ላይ ታዋቂ በማድረግ በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

Template by A4