ዜና - News
ተወዳጁ የኢሳት ጋዜጠኛ ንጉሴ ጋማ አረፈ
ክርስቲያኑ ማህበረሰብ ከሙስሊሙ ጋር እንዲተባበር ጥሪ ቀረበ
እስላሙም ወገናችን ክርስቲያኑን በመደገፍ፤ ክርስቲያኑም ወገናችን እስላሙን በመደገፍ ሁሉም እንዲነሳና ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪየን አቀርባለሁ” ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መልከጸዲቅ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. May 12, 2012)፦ በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መልከጸዲቅ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እደረሰ ያለውን አስከፊ ጭፍጨፋ በማውገዝ መላ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላለፉ።
መለስ ዜናዊ "የአፍሪካ መሪዎች ሙስና ውስጥ የምንገባው በስግብግብ ኩባንያዎች ጫና ነው" አሉ
በብራስልስ የአውሮፓ ኮሚሽን የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ
-
የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ እያደረሰ ያለውን የመብት ረገጣ እና እስራት በአስቸኳይ ያቁም!!
-
በኃይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባቱን እና ዜጎችን ማፈናቀሉን ያቁም!!
Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን 2004 ዓ.ም. May 10, 2012)፦”መብታችን ይከበር!” በሚል በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመደገፍና ”የኢህአዴግ መንግሥት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን የመብት ረገጣ፣ እስራት፣ በኃይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባቱንና ዜጎችን ማፈናቀሉን ያቁም!” በሚል መሪ መፈክር የፊታችን ሜይ 16 ቀን 2012 በብራስልስ የአውሮፓ ኮሚሽን ሕንፃ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ።
በሙስሊሞች ጉዳይ ውጥረቱ እንዳየለ ነው
የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር አዲስ መግለጫ አወጣ
Ethiopia Zare (አርብ ሚያዚያ 26 ቀን 2004 ዓ.ም. May 4, 2012)፦ "መንግስት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ውክልና የሌለውን የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባዔን በመጠቀም 'አህባሽ' የተባለውን አስተምህሮ በግድጅ ሊጭንብን እየሞከረ ነው " በሚል በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን መንግስት ዓላማውን ለማስፈጸም የሀይል እርምጃን መምረጡም ውጥረቱን ይበልጥ እያባባሰው መጥቷል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጤነኛ ነኝ አሉ
ጥርጣሬው እስካሁን አልቆመም
Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዚያ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. April 29, 2012)፦ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ከህዝብ ዕይታ ተሰውረው መቆየታቸውን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ታመዋል በሚል በኤርትራዊያን ዘንድ በስፋት መነጋገሪያ ሆነው ቢቆዩም በትላንትናው ዕለት በኤርትራ ቴሌቪዚን ቀርበው "ያስወሩብኝ ጠላቶቼ ናቸው" ሲሉ አስተባብለዋል።
ከፌዴሬሽኑ የተገነጠሉት ራሳቸውን “ዓሳ”AESA one ብለው ሰየሙ
EMF: (ዓርብ ሚያዚያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. April 27, 2012)፦ ከዋናው ፌዴሬሽን ተገንጥሎ ስሙን ESFNA One ብሎ የነበረው የነአያያ እና የነሰብስቤ ቡድን ትላንት እና ዛሬ ዲሲ ላይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ በዋና አጀንዳነት ከቀረቡት ጉዳዮች አንዱ የነበረው ባለፈው ሳምንት በቨርጂንያ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ነበር።
የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት ተባብሷል
አቶ መለስ ለውስጥ ችግራቸው ሁሉ ኤርትራን ተጠያቂ እያደረጉ ነው
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዚያ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. April 25, 2012)፦ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ባለፈው ማክሰኞ በተወካዮች ምክር ቤት ፪፭ኛ ጉባኤ ላይ " በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያያ በትግራይ ክልል ውስጥ በወርቅ ማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩ አንድ መቶ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶትን የኤርትራ መንግስት አፍኖ ወስዷቸዋል" ሲሉ መክሰሳተውን ተከትሎ የኤርትራ መንግስት " ይህ የተለመደ የፈጠራ ውንጀላ ነው።" ሲል አስተባብሏል።
በገዥው መንግሥት ላይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ ቀረበ
ጥሪውን ያቀረቡት አስራ ሁለት በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን ናቸው
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. April 19, 2012)፦ አስራ ሁለት በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን በጋራ በመሆን ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. (April 14, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአለም ደቻሳ ሁለት ልጆች አባት ተናገረ
ለልጆቹ የእናታቸውን መሞት መንገር እንዳስቸገረው ገለጸ
(ሊመለከቱት የሚገባ ቃለ ምልልስ)
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዚያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. April 10, 2012)፦ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ካውንስለር በራፍ ላይ ስትጎተትና ስትሰቃይ የነበረችውና በሊባኖስ ሆስፒታል ህይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አለም ደቻሳ የሁለት ልጆች አባት የሆነው ለሜሳ ኢጄታ ለልጆቹ የእናታቸውን መሞት ለመንገር እንደተቸገረ እንባ እየተናነቀው ጋርዲያን ለተባለው የዜና አውታር ገለጸ።
