ዋና ገጽ ዜና ዜና መኢአድ ሲቀሰቅስበት የነበረው መኪና ታሰረ
 
መኢአድ ሲቀሰቅስበት የነበረው መኪና ታሰረ Print E-mail

Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2001 ዓ.ም. December 01, 2008)፦ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ባለፈው ኀሙስ እና ዓርብ በአዲስ አበባ ከተማ ሲቀሰቅስበት የነበረው አይሱዙ መኪና ታሰረ።

 

ኀሙስ ዕለት ኅዳር 18 ቀን እና ዓርብ ኅዳር 19 ቀን የፓርቲው መሪ የሆኑትን የኢንጂንየር ኃይሉ ሻውልን ትልቅ ምስል በመጫን በድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ”ጃ ያስተሰርያል” በሚለው ዘፈን የሠላማዊ ትግል ጥሪ መልዕክት ለኅብረተሰቡ ሲያስተላልፍ የነበረው አይሱዙ መኪና የታሰረው ከዓርብ ዕለት ጀምሮ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። የመኢአድን ቅስቀሳ አስመልክቶ ባለፈው ሣምንት መዘገባችን አይዘነጋም።

 

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner