|
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2000 ዓ.ም. August 02, 2008)፦ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተካሄደው በአውሮጳ የስድስተኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ በተደረገው የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮ-ስዊድን ቡድን ከሎንዶኑ ካታንጋ ጋር ለፍፃሜ ደርሰው ኢትዮ-ስዊድን በቅጣትምት አራት ለሦስት አሸንፏል። ቡድኑ ከክብር እንግዶቹ አንዱ ከሆነው ከመንግሥቱ ወርቁ ዋንጫውን ወስዷል። (በፎቶግራፉ ላይ አቶ መንግሥቱ ወርቁ ለኢትዮ-ስዊድን የቡድን አንበል ዋንጫውን ሲሰጥ)
ውድ አንባብያት/ን በስዊድን ሀገር ስቶክሆልም ከተማ ለሁለት ቀናት የተደረገውን ፌስቲቫል በተመለከተ ልዩ ጥንክር አዘጋጅተን በቅርቡ ለንባብ እናበቃለን።
|