ዋና ገጽ ዜና ዜና በኦታዋ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩ አርበኞች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ
 
በኦታዋ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩ አርበኞች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ Print E-mail

ፎረም ኦታዋ ለሰብዓዊ መብትና ለዲሞክራሲ በሚል መጠሪያ የተሰባሰቡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ እስር ቤት ተጥለው በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ አርበኞችና ቤተሰቦቻቸው መርጃ የሚሆን ገንዘብ አሰባስበው ወደ አገር ቤት ላኩ።


የፎረሙ አባላት በእስር ላይ የሚገኙትን አርበኞች ለማስፈታት በኦታዋና አካባቢው የሚገኙትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ግንዛቤ እንዲያገኙ (ሎቢ) በማድረግ ወያኔ ከኢ-ሰብዓዊ ተግባሩ እንዲታቀብ ግፊት እንዲያደርጉ አጠንክረው በማሳሰብ ፤ ጐን ለጐንም የገንዘብ እርዳታውን ተከታታይነት ባለው ሁኔታ እንደሚቀጥሉ ታውቋል።


አያይዘውም ወያኔ በገዛ ህዝቡ ላይ በየጊዜው ከሚወስደው የአፈናና የእመቃ ተቃውሞ ባሻገር ኢትዮጵያን ለመታደግና ሥርዓቱን ለመገርሰስ የሚደረገው ርብርቦሽ ቀዳሚ መሆን እንደሚገባው በማመን ለዚሁ ተግባር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችው ጋር በመተባበር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner