ዋና ገጽ ዜና ዜና በአፋር ክልል ለታገቱት ጀርመናዊያን አርዱፍ ኃላፊነት ወሰደ
 
በአፋር ክልል ለታገቱት ጀርመናዊያን አርዱፍ ኃላፊነት ወሰደ Print E-mail

‘5ቱ ጎብኝዎች የሞቱት በኢትዮጵያ መንግስት ጥይት ነው’ አርዱፍ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. January 23, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት ለ5 ጎብኝዎች ሞት ምክንያት ለሆነው እና ለ27 ጎብኝዎች ላይ ለተቃጣው ጥቃት በህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ ወታደሮችና በአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) መሀከል በተነሳ ጦርነት መሆኑንና ታጋቾቹ ሁለት ጀርመናዊያን በእጁ እንደሚገኙ አርዱፍ አስታወቀ።

 

አርዱፍ ቅዳሜ ጃንዋሪ 21 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በውጊያው 16 የመንግስት ወታደሮች መሞታቸውንና 12 የሚሆኑትን ደግሞ ማቁሰሉን የገለጸ ሲሆን ቁጥራቸውን ያልገለጻቸው ወታደሮችም በቁጥጥሩ ስር የሚገኙም ገልጿል።

 

የሞቱት አምስት ጎብኝዎች በወያኔ መንግስት ወታደሮች በተተኮሰ ጥይት መሆኑን ገልጾ ሁለቱ ጀርመናዊያንም ሆኑ በቁጥጥሬ ስር አሉ የመንግስት ወታደሮች በጤናና በምቹ ሁኔታ ነው ያሉት ሲልም አብራርቷል።

 

ከአፋር ሽማግሌዎች ጋር ሰላማዊ ድርድር ከተደረገ በኋላ ታጋቾቹ ይለቀቃሉ ያለው አርዱፍ መግለጫ ጥቃቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ እጅ አለበት ሲል መክሰሱ አግባብነት እንደሌለውና በእኛና በወያኔ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች መሀከል የተደረገ ውጊያ እንጂ የኤርትራ መንግስት እጅ የለበትም ብሏል።

 

ኤርትራ የአፋር አማጺያንን ታስታጥቃለች፤ ታሰለጥናለች የሚለው ክስ መሰረተ ቢስ የሆነና ውሸት ነው ብሏል የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ባወጣው መግለጫ።

 

አርዱፍ “የንጹሀን ሰላማዊ ሰዎች ህይወት በመጥፋቱ ልባዊ ሀዘን ተሰምቶናል። ለሟቾቹ ቱሪስቶች ቤተሰቦችና ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን” ብሏል።

 

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ስለተገደሉትም ሆነ ስለታገቱት የመንግስት ወታደሮች ትንፍሽ ሳይል አውሮፓዊያን ጎብኝዎችን ብቻ ማንሳቱን በተመለከተ አርዱፍ የራሱን ወንጀለኞች ሸሽጎ እኛን ወንጀለኛ አስመስሎ ለማቅረብ፣ (ህጋዊውን) ተገቢውን የፖለቲካ ጥያቄያችንን ህገ ወጥ ለማስመሰል እንዲሁም በክልሉ ያለውን የአፋር ህዝብ ‘ሽብርን ለመዋጋት’ በሚል ሰበብ ይብሱኑ ለማሸበር በማሰብ ነው። በሚል ምክንያት ያሉትን ደርድረዋል።

 

የአፋር አማጺያን ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዜያት ሰባት ጊዜ ያህል በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን ማገታቸው ሲታወስ ሁሉንም አንዳች ጉዳት ሳይደርስባቸው መልቀቃቸው ይታወቃል።

 

በ2007 ዓ.ም የአማጺው ኃይል ታጣቂዎች 5 አውሮፓዊያንና ስምንት ኢትዮጵያዊያንን አግቶ አውሮፓዊያኑ ታጋቾች ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጎዜ ውስጥ ለኤርትራ መንግስት በማስረከብ በነጻ እንደለቀቃቸው ይታወቃል። ስምንቱ ኢትዮጵያዊያን ግን ለሁለት ወራት ያህል ቆይተው ነበር የተለቀቁት።

 

በወቅቱ የእንግሊዝ መንግስት አውሮፓዊያኑ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ኤርትራ ረድታናለች ብለው እንደነበርም አይዘነጋም።

 

 

 

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner