Home ዜና Latest የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ ከአ.አ. ጎንደር ተወስዶ ታሰረ
የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ ከአ.አ. ጎንደር ተወስዶ ታሰረ PDF Print E-mail
Monday, 25 August 2008 12:56

Amare Aregawi, Publisher & Editor-in-chief of Reporter Ethiopia Zare (ሰኞ ነኀሴ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. August 25, 2008)፦ በሀገር ውስጥ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ የሚታተመው የ”ሪፖርተር” ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ አቶ አማረ አረጋዊ ዓርብ ነኀሴ 16 ቀን ከቢሮው ተወስዶ ጎንደር ውስጥ በእስር ላይ እንደሚገኝና ዛሬ ሰኞ ነኀሴ 19 ቀን ጎንደር ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

 

አቶ አማረ ከዓርብ ነኀሴ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 22, 2008) ጀምሮ ጎንደር ውስጥ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለእስሩ መነሻ የሆነው ዳሽን ቢራን አስመልክቶ በሪፖርተር የአማርኛ ጋዜጣ ላይ በጋዜጣው ሪፖርተር ተሾመ ንቁ የተዘገበው ዜና መሆኑ ታውቋል።

 

ከዚህ ቀደም አቶ ተሾመ ንቁን ሁለት ደኅንነቶች ከሪፖርተር ቢሮ በመውሰድ ጎንደር ካሰሩት በኋላ በዳሽን ቢራ ዘገባ ምክንያት ፍርድ ቤት አቅርበውት ነበር። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መመልከት ያለበት የፌደራሉ ፍርድ ቤት መሆኑንና እዚያ አዲስ አበባ ሊከሱትና ፍርድ ቤት ሊያቀርቡት እንደሚችሉ በመግለጽ ተሾመን በነፃ አሰናብቶት ነበር።

 

በወቅቱ ከእስር ሲለቅ እንደደንቡና ሕጉ የወሰዱት ከአዲስ አበባ ስለሆነ ሊመልሱት ሲገባ እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ ለቅቀውታል።

 

የዳሽን ቢራ የቦርድ ዳይሬክተር አቶ በረከት ስምዖን ሲሆን፣ አቶ በረከት ስምዖን በሚኒስቴር ማዕረግ የጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የህዝብ ግንኙነት ልዩ አማካሪና የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስትር እንደነበር ይታወቃል። አቶ በረከት የጠ/ሚ/ር መለስ ቀኝ እንደሆኑ ይነገራል።

 

 

ተያያዥ

 
Andenet in Europe, Nov, 2008