|
Thursday, 21 August 2008 22:04 |
|
Ethiopia Zare (ኀሙስ ነኀሴ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. August 21, 2008)፦ በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የአንድነት ለዴሞክራሰና ለፍትህ ፓርቲን ዓላማ ለኢትዮጵያኖች ሲያስረዱና ከህዝብ ጋር ውይይት ሲያካሂዱ የነበሩት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም እና አቶ አስራት ጣሴ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸውን ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ አስረዳ።
ዛሬ ማምሻውን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ ወደ ሃያ የሚሆኑ ሰዎች አቶ አስራት ጣሴን እና ፕ/ር መስፍንን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል። አቶ አስራት ጣሴ የአንድነት ፓርቲ መስራች እና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ ሲሆኑ፣ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ደግሞ የአንድነት ፓርቲ መሥራች እና የፓርቲው ም/ቤት አባል መሆናቸው ይታወቃል። |