Home ዜና ዛሬ ለቴዲ አፍሮ ወሳኝ ቀን ነው
ዛሬ ለቴዲ አፍሮ ወሳኝ ቀን ነው PDF Print E-mail
Sunday, 20 July 2008 23:41

Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. July 21, 2008)፦ የብዙዎችን ቀልብ ገዝቶ የቆየው ታዋቂውና ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሦስት ወራት የእስር ቆይታ በኋላ በአወዛጋቢው የምኒልክ ሆስፒታል የሰነድ ማስረጃ የዓቃቤ ሕግ ክርክር ተደምድሟል። ፍርድ ቤቱም በዛሬው ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል።

 

በአቃቤ ሕግ የቀረበው ማስረጃ ክሱን አያስረዳም ወይም በቂ አይደለም ብሎ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቴዲን በዕለቱ በነፃ የሚያሰናብተው ይሆናል።

 

በሌላ በኩል የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ድርጊቱ ስለመፈጸሙ አጠራጣሪ ሆኖ ተገኝቷል ካለ “ተከላከል” የሚል ብይን የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህ ማለት ቴዲ አፍሮ የሚቀጥሉትን … ወራት በማረሚያ ቤት ሆኖ የመከላከያ ማስረጃውን ያቀርባል ማለት ነው።

 

የዛሬው ችሎት እስከዛሬ ከነበሩት የችሎት ቀጠሮዎች ሁሉ ለቴዲ አፍሮ ወሳኝ ቀን ይሆናል።

 

 

ተያያዥ

 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ