ዋና ገጽ ዜና ዜና አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩን መረጠ
 
አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩን መረጠ Print E-mail
Wednesday, 18 June 2008 18:52

ወ/ት ብርቱካን የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙ ታወቀ።

 

ድርጅቱ አራት የምክትል ሊቃነመናብርት የመረጠ ሲሆን፣ የድርጅት ጉዳይና ምክትል ሊቀመንበር ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራሁ፣ የውጭ ጉዳይና ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ የህዝብ ግንኙነትንና ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፣ የፋይናንስና የአስተዳደር እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ዘውዴ፣ የተመረጡ ሲሆን፣ አቶ አስራት ጣሴን የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ በማድረግ የሾመ መሆኑ ታውቋል።

 

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!