Home ዜና የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በኑርንበርግ ህዝባዊ ስብሰባ ክፍል ፩
የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በኑርንበርግ ህዝባዊ ስብሰባ ክፍል ፩ PDF Print E-mail
Saturday, 14 June 2008 08:15

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. June 14, 2008)፦ ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ ከደጋፊዎቹና ከኢትዮጵያውያን የሚያደርገውን ህዝባዊ ውይይት መጀመሩ ታወቀ። በዚህ ህዝባዊ ውይይት የንቅናቄው መሥራቾች የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ መስፍን አማን እንደተገኙ ታውቋል።

 

በዚህ ህዝባዊ ውይይት ላይ የመጀመሪያው ተናጋሪ የነበሩት አቶ መስፍን አማን ሲሆኑ፣ በመቀጠል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ንግግር አድርገዋል። ስብሰባው እረፍት አድርጎ ከተመለሰ በኋላ ከተሰብሳቢው ጋር ሰፊ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

 

ውይይቱ በተለይም በፓልቶክ የኢትዮጵያን ከረንት አፌርስ ዲስከሽን የውይይት መድረክ ክፍል በቀጥታ እየተላለፈ ሲሆን፣ የአቶ መስፍን አማንን ንግግር ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ቀሪውን ውይይት በድምፅ ለማቅረብ እንሞክራለን።

 

ንግግሩን ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን (Play Button) ይጫኑ!

 

 
 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ