Home ዜና ፖሊስ በአንድነት ጽ/ቤት ጉባዔው እንዳይካሄድ ከለከለ (7፡40 ሰዓት)
ፖሊስ በአንድነት ጽ/ቤት ጉባዔው እንዳይካሄድ ከለከለ (7፡40 ሰዓት) PDF Print E-mail
Saturday, 14 June 2008 02:57

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. June 14, 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መሥራች ጉባዔውን ለማድረግ ዛሬ ጠዋት በኢምፔሪያል ሆቴል ሊያደርገው ያቀደውን ጉባዔ ፖሊስ ያስተጓጎለው ሲሆን፣ በመቀጠልም በፓርቲው ጽሕፈት ቤት ከሰዓት በኋላ ሊካሄድ የነበረውን ስብሰባ ፖሊስ ጽ/ቤቱን በመክበብ ተሰብሳቢዎቹ ቅጽር ግቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ እየሰጠ መሆኑን ከስፍራው ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ አስረዳ።

 

ከስፍራው በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 7፡45 ሰዓት (1፡45 PM) ላይ ፖሊስ ተሰብሳቢዎቹን “ግቢውን ለቅቃችሁ ውጡ!” እያላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል።

 

ከኢትዮጵያ ዛሬ፦ ተጨማሪ ሪፖርት በተቻለን ፍጥነት አጠናክረን እናቀርባለንና፤ ትንሽ ቆይተው ተመልሰው እንዲጎበኙን እንጠይቃልን።

 

 
 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ