ዋና ገጽ ዜና ዜና አንድነት ግንቦት 23 ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል
 
አንድነት ግንቦት 23 ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል Print E-mail
Monday, 19 May 2008 21:48

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2000 ዓ.ም. May 19, 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ትናንት ባካሄደው የላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባው ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን ለመጥራት መወሰኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጡ።

 

እስካሁን ድረስ ከምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከቻ ያላስገባውና በወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቀድሞው የቅንጅት ፓርቲ፣ የአሁኑ የ”አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ” ግንቦት 23 በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የድርጅቱን አመራሮች እንደሚመርጥ ይጠበቃል።

 

ጠቅላላ ጉባዔው ተካሂዶ ካበቃ በኋላ ፓርቲው ሕጋዊ ፈቃድ ይሰጠው ዘንድ ለምርጫ ቦርድ ማመልከቻውን ያስገባል ተብሎ ይጠበቃል።

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!