Home ዜና Latest ቴዲ አፍሮ ዛሬ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ገባ
 
ቴዲ አፍሮ ዛሬ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ገባ Print E-mail
Wednesday, 16 April 2008 19:06

Teddi Afro

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. April 16, 2008) ዝነኛው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከዚህ ቀደም "በመኪና ሰው ገለህ አምልጠሀል" በሚል ተከሶበት በነበረው ክስ ምክንያት የፌደራል ዓቃቢ ሕግ የዋስትና መብት ሊሰጠው አይገባም በማለቱ የዋስ መብቱን በሚመለከት ውሳኔ እስኪሰጥ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት የተላከ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።

 

 

Teddi Afro in Stockholmበዛሬው ዕለት በቴዲ ላይ የቀረበበት ክስ ያለመንጃ ፍቃድ በመንዳት እና ሆን ብሎ ሰው ገድሎ በማምለጥ ክስ ነው። ጠበቃው አቶ ሚሊዮን አሰፋ "ደንበኛዬ ቴዎድሮስ ካሳሁን ድርጊቱን ካለመፈጸማቸውም በላይ ክሱ ሊቀየር ይገባዋል" ሲሉ የተከራከሩ ሲሆን፣ ዳኛ ልዑል ገ/ማሪያም የፌዴራል ዓቃቢ ሕግ እና ጠበቃው ያቀረቡትን ክርክር ካዩ በኋላ ውሳኔ ለመስጠት ለመጭው ሰኞ ቀጠሮ በመስጠት ተከሳሽ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቀጠሮው እስኪደርስ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲቆይ የተወሰነ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

 

 

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ለአራት ሰዓታት ያህል ፍርድ ቤቱ አካባቢ በሚገኘው ማቆያ እስር ቤት በእስር ከቆየ በኋላ ወደ ቃሊቲ መውረዱን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

 

 

ዳኛው አቶ ልዑል ገ/ማሪያም የቅንጅት መሪዎችን ክስ ካዩት ዳኞች መካከል የቀኝ ዳኛ ሆነው ተሰይመው የነበሩ ሲሆን፣ በአስቸጋሪነታቸው የሚታወቁ ከመሆኑም በላይ፤ ዛሬ በቴዲ አፍሮ ላይ የቀረበበትን ክስ የዋስትና ውሳኔ ዛሬውኑ መወሰን ይችሉ እንደነበር ታዛቢዎች ይናገራሉ።

 

ተያያዥ

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች