Home ዜና Latest የአንድነት ምክር ቤት አባል በመከላከያ መኪና ተገጩ
 
የአንድነት ምክር ቤት አባል በመከላከያ መኪና ተገጩ Print E-mail
Wednesday, 07 April 2010 23:53

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ.ም. April 7, 2010)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዳዊት አስራደ፤ በመከላከያ ሠራዊት መኪና ተገጭተው በእግራቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታወቀ።

 

ከአንድ ሣምንት በፊት በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ አዲስ አበባ ከተማ እንጦጦ አካባቢ ከተገጩ በኋላ ወንጀሉን የፈጸሙት አካላት ማንነት ካለመታወቃቸውም ሌላ ምን አይነት እርምጃ እንደተወሰደባቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

 

አቶ ዳዊት አስራደ አደጋው ከደረሰባቸው ጀምሮ በዮርዳኖስ የግል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ፓርቲያቸው አስታውቋል።

 

በአቶ ዳዊት ላይ ለደረሰው የመኪና አደጋ “የገዢው ፓርቲ እጅ አለበት” የሚሉ ወገኖች እስካሁን ምንም አይነት ፍንጭ አለመገኘቱን ገልጸዋል። የመኪና አደጋው የደረሰባቸው የአንድነት ም/ቤት አባል በእግራቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
የረቡዕ ግጥም ቁጥር ፮

መጀመሪያ ለራስህ ነፃነት ስጥ

ከሱ አገኛለሁ ብለህ አትለማመጥ

መብትህን እራስህ ሳትጠብቅ

አትገረም በእሱ መንጠቅ