ዜና - News

በየመን የኤምባሲ ተወካዮች ተዋርደው ከቤተክርስቲያን ወጡ... Print E-mail
Thursday, 09 February 2012 02:02

በግሩም ተ/ሀይማኖት

ሀበሻ በየመን ክፍል 10

የምጀምረው በሁለት አሳዛኝ ዜና ነው፡፡ የመን ውስጥ ከሚታተሙት የግል ጋዜጣዎች አንዱ የሆነው አል-ሻራዕ የተባለው 21/1 2012 ዕትሙ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ በሚል የያዘውን ዘገባ ተርጉሜ እንደሚከተለው አስነብባለሁ። በዚህ ሰሞን በባህር ወደ የመን ከገቡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል ሰላሳ የሚሆኑትን ወደ ሳዑዲ ለመውሰድ የጫናቸው መኪና ላይ በተከፈተ ተኩስ ሶስቱ ሲሞቱ የመናዊ ሾፌሩን ጨምሮ የቆሰሉም መኖሩ ተረጋገጠ፡፡ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምንም አይነት መረጃ ካልተገኘላቸው ሟቾች ጋር ከነበሩት መካከል አምስት የሚሆኑትን ደግሞ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። የሟቾቹ ኢትዮጵያዊነትም የተረጋገጠው አብረዋቸው ካሉት ተጓዦች ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

በጋምቤላ የምስጢር ደኅንነት ሠራተኛው ተገደሉ - (አኢጋን) Print E-mail
Sunday, 05 February 2012 18:03

በጋምቤላ ክልል በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ይሠራሉ የተባሉት አቶ ጌታቸው አንኮሬ ባልታወቁ ሰዎች በድንገት መገደላቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል በክልሉ የነበረው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ መባባሱ ተገለጸ። የክልሉ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችም ስጋት ላይ ወድቀዋል።


የደቡብ ክልል ተወላጅና የህወሃት አባል በመሆን በክልሉ ለረዥም ዓመታት በምስጢር የደኅንነት ሠራተኛነታቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ጥር 24 ቀን 2012 .. አመሻሽ ላይ ህይወታቸው ያለፈው በፕሬዚዳንቱ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኖሪያ ቤት ውስጥ ስብሰባ ላይ ቆይተው የመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ውስጥ እንደገቡ ነው።

 

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የመረጃ ምንጮች ከስፍራው እንዳስታወቁት የአቶ ጌታቸው ህይወት ሊያልፍ የቻለው በመኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ባልታወቁ ሰዎች በተደጋጋሚ በጥይት ከተደበደቡ በኋላ ነው። በከተማዋ እምብርት ግድያውን ያከናወኑት ክፍሎች ለምን ጥቃቱን እንደፈጸሙ ከየትኛውም ወገን በግልጽ የተነገረ ነገር የለም።

 

ከሰባት ዓመታት በፊት ማንነታቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች የክልሉን እስር ቤት ሰብረው በመግባት የፖሊስ ኮሚሽነሩን ዲድዑሞ ኦሞኒ በመግደል የሚፈልጉዋቸውን እስረኞች ካስፈቱ በኋላ በጋምቤላ ከፍተኛ የደኅንነት ኃላፊ ሲገደሉ አቶ ጌታቸው የመጀመሪያ ናቸው። በወቅቱ እስረኞቹን ለማስፈታት የፖሊስን ጥበቃ አልፈው የገቡት ኃይሎችሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል አልመጣንምበማለት ጥበቃ ላይ የነበሩትን ማረጋጋታቸውን ምስክሮች በወቅቱ መናገራቸውን ምንጮቻችን አስታውሰዋል።

 

አሁን የተከሰተው ግድያ በጋምቤላ እየተካሄደ ካለው የመሬት ነጠቃና አስገድዶ ማፈናቀል ጋር ስለመያያዙ ኃላፊነት ወስዶ የተናገረ አካል አስካሁን አልተሰማም። የጋራ ንቅናቄያችን የመረጃ ምንጮች ያሰባሰቡት አስተያየት በክልሉ በህወሃት/ኢህአዴግ አማካኝነት እየተከናወነ ያለው ኢሰብዓዊነት የተሞላው የመሬት ነጠቃና የግዳጅ ሰፈራ የፈጠረው የእምቢተኛነት ውጤት ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

 

ከግድያው በኋላ የአገዛዙ ታጣቂዎች፣ የፌዴራል ፖሊስ ኃይሎችና ወታደሮች ገዳዮቹን በአሰሳ ለማግኘት ሲዋከቡ ታይተዋል። የዓይን ምስክሮችን ዋቢ ያደረጉት የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ይህ ዜና እስከተቀናበረበት ሰዓት ድረስ ግድያውን ስለሰነዘሩት ክፍሎች የተገኘ ፍንጭ ስለመኖሩ የክልሉ ፖሊስ የሰጠው መግለጫ የለም። የፌዴራሉ ኃይሎች ሶስት ያካባቢው ተወላጆችና ሁለት የሌላ አካባቢ ሰዎች በጥርጣሬ ይዘዋል።

 

በክልሉ ያለው ውስብስብ ችግርና የአቶ ጌታቸው ግድያ የፈጠረው ስጋት ከፍተኛ በመሆኑ የጋምቤላ ከተማ በወታደሮች ጥበቃ ስር እንድትውል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር። ሆኖም ግን የጸጥታ ሠራተኞች ፕሬዚዳንቱ በቃል ያስተላለፉትን ትእዛዝ በደብዳቤ ያረጋግጡ በመባሉ ለጊዜው ተጨማሪ ወታደሮች ሳይመደቡ ቀርቷል። ተጨማሪ ሃይል እስኪታዘዝ በሚል ጊዜያዊ የሰዓት እላፊ ተጥሎ እንደነበር ባልደረቦቻችን ከስፍራው አስታውቀዋል።

 

ይኸው ካድሬዎችንና የአገዛዙን አገልጋዮች ጭንቀት ውስጥ የከተተው አደጋ በኦሞ ጨለቆ አቦቦ አካባቢና በሌሎች ወረዳዎችም አለመረጋጋት በመፍጠሩ ለካድሬዎችማንንም አትመኑየሚል መመሪያ ከበላይ አካላት መሰጠቱ ታውቋል።

 

በክልሉ እየጠፋ ያለው የሰው ህይወትና ንብረት እንዲሁም አለመረጋጋት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄን እጅግ እንደሚያሳስበው ገልጾህዝብን አለማዳመጥ፣ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ አለመገዛት፣ ዜጎችን እትብታቸው ከተቀበረበት መሬት በግዳጅ በማፈናቀል መሬታቸውን የመሸጥ ዘመቻ ማካሄድ የክልሉን ነዋሪዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳዘነ በመሆኑ ለሚደርሰው ችግር ሁሉ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተጠያቂ ነውበማለት ለሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ክፍላችን አስታውቋል። በሌላም በኩል የክልሉን ተወላጆችሽፍታበማለት የተጀመረው ወከባ ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንደሚያስከትል አኢጋን ስጋቱን ገልጾዋል።

 

በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ያለፈው አቶ ጌታቸው አስከሬናቸው ወደ ትውልድ አገራቸው ሆሳዕና በነጋታው መላኩን የአይን ምስክሮች አስታውቀዋል። አቶ ጌታቸው የሆሳዕና አካባቢ ተወላጅ ሲሆኑ፣ ወደ ጋምቤላ የመጡት በቀድሞው ስርዓት የሰፈራ ፕሮግራም በህጻንነታቸው ነበር። የሚያውቋቸው እንደሚናገሩት አቶ ጌታቸው በክልሉ የምስጢር የደኅንነት ሠራተኛ ሆነው ለረዥም ዓመታት ከመስራታቸው በተጨማሪ ከፌዴራሉ የስለላ መዋቅር ጋር በቀጥታ ግንኙነት ነበራቸው። በተለይም አቦቦ አካባቢ ሰፋፊ መሬት ከወሰዱ የውጪ ባለሃቶች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ጌታቸው ቤተሰቦቻቸውም ጭምር የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ አገልጋዮች እንደሆኑ ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። በክልሉ አንድ ነባር የፖሊስ አባል እንደተናገሩትሟች በታችኛው የቀበሌ አስተዳደር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሰላይ ፖለቲከኛና ትልቅ የተባለ የገንዘብ አቅም አላቸውበማለት አስረድተዋል።

 

ባለፈው ሳምንት ፉኚዶ ከተማ በሚገኘው የወታደር ካምፕ ውስጥጸጉረ ልውጦች ታይተዋልበሚል በድንገት በተከፈተ የተኩስ እሩምታ ሶስት ሰዎች በተኙበት ህይወታቸው ሲያልፍ፣ እናቷን ያጣች አንዲት ታዳጊና በሊስትሮ ስራ የተሰማራ አንድ ወጣት መቁሰላቸውን የክልሉን ምንጮቻችንን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። በዘገባው በንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ባደረሱት ላይ ፖሊስና የክልሉ ባለስልጣናት ምንም ዓይነት ርምጃም ለመውሰድ አለመሞከራቸው ነዋሪዎቹን ክፉኛ እንዳሳዘነ ተዘግቦ ነበር። ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ በክልሉ መስተዳድር በኩል ኃላፊነትን መውሰድ አስመልክቶ የተሰጠ ነጻ መግለጫ የለም፡፡

 

ከስምንት ዓመታት በፊት በጋምቤላ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን በአቶ መለስ ትዕዛዝና በአቶ ኦሞት ኦባንግ አስፈጻሚነት ከተጨፈጨፉና በሺዎች የሚገመቱ ከተሰደዱ በኋላ በቅርቡ አቶ ኦሞትን ከሥልጣን ለማስወገድና ለማሰር በተካሄደ ግምገማ ላይ አቶ ኦሞትእኔ ከታሰርኩ ወታደርና መሣሪያ የሰጠኝ አቶ መለስም ይታሰራልበማለት አቶ መለስን የዕልቂቱ ቀጥተኛ ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ክስተት በኋላም ሁኔታውን በማስተባበል ከህወሃት/ኢህአዴግ በኩል ምላሽ አለመሰጠቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዓለምአቀፉ ፍርድቤት አቶ መለስን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስከሰስ እየታገሉ ለሚገኙት የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት፣ አኢጋን እና ሌሎች ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉት እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)

_____________________________________

ለተጨማሪ መረጃ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነትን ( This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org) በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ፡፡

 

በሱማሊያ የኢትዮጵያ ጦር ሰፈር በአጥፍቶ ጠፊዎች ተጠቃ! Print E-mail
Thursday, 26 January 2012 04:06

አልሸባብ 10 ወታደሮች ገደልኩ ብሏል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2004 ዓ.ም. January 25, 2012)፦ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ሰፈር ላይ የአልሸባብ አጥፍቶ ጠፊ በሚኒባስ ሙሉ የታጨቁ ቦምቦች ማፈንዳቱ ተዘገበ። በጥቃቱ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮች መግደሉን አልሸባብ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

በአፋር ክልል ለታገቱት ጀርመናዊያን አርዱፍ ኃላፊነት ወሰደ Print E-mail
Monday, 23 January 2012 19:57

‘5ቱ ጎብኝዎች የሞቱት በኢትዮጵያ መንግስት ጥይት ነው’ አርዱፍ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም. January 23, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት ለ5 ጎብኝዎች ሞት ምክንያት ለሆነው እና ለ27 ጎብኝዎች ላይ ለተቃጣው ጥቃት በህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ ወታደሮችና በአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) መሀከል በተነሳ ጦርነት መሆኑንና ታጋቾቹ ሁለት ጀርመናዊያን በእጁ እንደሚገኙ አርዱፍ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ከጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ‹‹ትግላችን›› ጋር… Print E-mail
Saturday, 21 January 2012 20:53

ተመስገን ደሳለኝ

ማን ይፈራል ሞት

ማን ይፈራል

ለእናት ሀገር ሲባል..

የጊዜው ወታደራዊ ደርግ አስተዳደር፣ የአብዮታዊ ጦር ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ፣ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ዋና ፀሀፊ፣ የኢህዴሪ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት… ጓድ መንግስቱ ኃ/ማርያም ሰሞኑን በስደት ከሚኖሩበት ዙምባቤ ‹‹ትግላችን›› የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመው በ39 የአሜሪካ ዶላር እየቸበቸቡ ነው። በእርግጥ ሀገር ከመሸጥ መጽሐፍ መሸጥ የተሻለ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

በአፋር ክልል የተገደሉት ጎብኝዎች ዜግነት ታወቀ Print E-mail
Wednesday, 18 January 2012 21:44

4 ሰዎች ታግተዋል፣ ሁለት ቆስለዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)ትላንት ማክሰኞ ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ  በአፋር ክልል ያልታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ የተገደሉት አምስት ጎብኝዎች ዜግነት መረጋገጡ እና አራት ሰዎች መታገታቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

70ሺህ ኢትዮጵያዊያን በግዳጅ ተፈናቀሉ Print E-mail
Wednesday, 18 January 2012 21:19

አስገድዶ መድፈርና ከፍተኛ የመብት ረገጣ ተፈጽሞባቸዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ በኢትዮጵያ ለም የሆኑ የእርሻ መሬቶችን ለኢንቨስትመንት ለመስጠት መንግስት በያዘው ፕሮግራም ሳቢያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች በግዳጅ እየተነሱ ለኑሮ ተስማሚ ወዳልሆኑ ቦታዎች መወሰዳቸውን ሂዩማን ራይትስ ወች አጋልጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት የሶማሌን ባለስልጣናትን ማሰራቸው ተገለጸ Print E-mail
Wednesday, 18 January 2012 20:19

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ሁለቱ ባለስልጣናት የታሰሩት እሁድ ከሰዓት የሰላም ስምምነቱን ካፈረሱ በሁዋላ መሆኑን ሶማልላንድ ፕሬስ ዘግቡዋል። የታሰሩት ባለስልጣናት አደን አብድላሂ አወል የሱማሌ ክልል አኩ ሱና ፓርላማ ቡድን መሪ እና አብዱልፈታህ ሀሰን ጃማ የሸበሌ ቫሊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት መሆናቸው ታውቋል

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የኢትዮጵያ ባንኮች ተቀማጭ ገንዘባቸው በመቀነሱ ትርፋቸውም መቀነሱ ተገለጸ Print E-mail
Wednesday, 18 January 2012 20:15

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ብሉምበርግ የአክሰስ ካፒታል ሼር ካምፓኒን ጠቅሶ እንደዘገበው በዚህ አመት የኢትዮጲያ ባንኮች ትርፋቸው እየቀነሰ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ህጉ አበዳሪዎች ከመንግስት የዋስትና ሰነድ (ሴኩሪቲ)እንዲገዙ ስለሚጠይቅ መሆኑን ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

በአፋር ክልል አምስት የውጭ ሀገር ዜጎች በታጣቂዎች ተገደሉ Print E-mail
Wednesday, 18 January 2012 07:45

አቶ በረከት ኤርትራን ተጠያቂ አድርገዋል

ሁለት ጀርመናዊያን ተጠልፈዋል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. January 17, 2012)፦ ባለፈው ሰኞ  ማምሻው ላይ በአፋር ክልል ይንቀሳቀሱ በነበሩ የጎብኝዎች ቡድን ላይ ማንነታቸው ያልተረጋገጠ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ 5 ሰዎች መሞታቸውና ሁለት ሌሎች ቱሪስቶች ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 
«StartPrev12345678910NextEnd»

Page 1 of 85

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!