ዋና ገጽ ቃለምልልስ ቃለምልልስ
 
ቃለምልልስ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ቪዲዮ) Print E-mail
User Rating: / 69
PoorBest 

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ”የሣምንቱ እንግዳ” በተሰኘው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት) ዝግጅት ላይ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ከሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ከ80 ደቂቃ በላይ የፈጀ ቃለ-ምልልስ አድርጓል። ይህ ቃለ-ምልልስ ክፍል አንድ ሲሆን፣ በምርጫ 97፣ በሽምግልና፣ ... በጠቅላላው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያጠነጥናል። ለመመልከትና ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!

 

ባለ ሐይኩ ሲጠየቅ Print E-mail
User Rating: / 13
PoorBest 

ሰሞኑን BETSY AND THE SUPERCOPTER በሚል ርእስ አዲስ መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለኅትመት በቅቷል። ደራሲው ዓለማየሁ ታዬ ከዚህ ቀደም ባሳተማቸውና “የዓለማየሁ ሩባያት”፤ “ግራፊቲ” እና “ሐይኩ” በተሰኙ የግጥም መድበል መጽሐፎች እንዲሁም “ጣፋጭ ተረቶች” በሚል ርእስ ባሳተመው ትርጉም የህጻናት መጽሐፍ እናውቀዋለን። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በህንድ ፑኔ ዩኒቨርስቲ በሥነጽሁፍና ሳይኮሎጂ አሁንም በአሜሪካ የተለያዩ ኮሌጆች ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው ዓለማየሁ ታዬ ኢትዮጵያ ውስጥ በሬዲዮና በኅትመት ጋዜጠኝነት ሰርቷል። በአሁኑ ወቅት በሎስ አንጀለስ ከተማ ቪሌጅ ግሌን ዌስት በተሰኘ ትምህርት ቤት በረዳት አስተማሪነት /Teacher’s Aide/ በመስራት ላይ ይገኛል። የአዲሲቱ መጽሐፍ ለኅትመት መብቃት ምክንያት ሆኖት ታሪኩ ኃይሉ በገጣሚው ስራዎች ላይ ከገጣሚው ጋር ያደረገውን ሰፋ ያለ ቃለምልልስ እነሆ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሲኤንኤን ጋር Print E-mail
User Rating: / 26
PoorBest 

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም. May 25, 2011)፦ የሲፒጄን “የዓለም አቀፍ ፕሬስ ነፃነት ሽልማት” አሸናፊ የሆነውን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን ሲኤንኤን “አፍሪካን ቮይስስ” በተሰኘው ፕሮግራሙ ላይ ቃለምልልስ አድርጎለታል። ፕሮግራሙ የተላለፈው ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. (ሜይ 24 ቀን 2011 እ.ኤ.አ.) ሲሆን፤ በዚህ ቃለምልልስ ጋዜጠኛ ዳዊት ስለራሱ፣ ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ምን እንደሚመስል፣ ተመዘገበ ስለተባለው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ … በአጠቃላይ በሀገሪቱ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ሰፋ አድርጎ አብራርቷል። ጋዜጠኛ ዳዊት የ“አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ መሆኑ ይታወቃል። ቃለምልልሱ ሦስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ “ሙሉውን አስነብበኝ …” የሚለውን በመጫን ቀሪዎቹን መመልከት ይችላሉ። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ)

ክፍል ፩

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 
«StartPrev1234567NextEnd»

Page 1 of 7

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ