|
|
|
Wednesday, 23 July 2008 11:10 |
|
ድጋፍ አሰባሳቢዎቹ መልስ አላቸው በኢ/ር ኃይሉ ሻውል የሚመራው ቡድን ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን እና እሁድ ሰኔ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔ አድርጎ አመራሮቹን መምረጡ አይዘነጋም። በጠቅላላው ጉባዔ ም/ፕሬዝዳንትና የሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት አቶ አባይነህ ብርሃኑ፤ የጉባዔው መዝጊያ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። |
|
Read more...
|
|
|
|
|
Wednesday, 23 July 2008 03:42 |
|
የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የቀድሞ ም/ሊቀመንበርና፤ ቅንጅት አዲስ አበባን ተረክቦ ቢሆን ኖሮ ለአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባነት ተመርጦ የነበረው ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ በተለይ በሀገር ውስጥ ባሉ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኀን ግንቦት 7 ንቅናቄን እንደተቀላቀለ ተደርጎ የሚናፈሰውን ወሬ አስመልክቶ በሀገር ውስጥ የሚታተመው የእንቢልታ ጋዜጣ ቃለምልልስ አድርጎለታል። |
|
Read more...
|
|
|
|
Saturday, 12 April 2008 09:28 |
|
ከአቶ ዳንኤል በቀለ እና ከአቶ ነፃነት ደምሴ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. April 12, 2008)፦ መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ከእስር የተፈቱት የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች አቶ ዳንኤል በቀለ እና አቶ ነፃነት ደምሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለእራሳቸው፣ ስለቤተሰቦቻቸው፣ ስጓደኞቻቸው፣ ስለሥራዎቻቸው፣ ስለእስሩ፣ ስለክሱና የፍርድ ሂደቱ፣ … ሀገር ውስጥ ከሚታተመው እንቢልታ ለተሰኘው ሣምንታዊ ጋዜጣ ቃለምልልስ ሰጡ። የአቶ ነፃነት ደምሴ እህት ወ/ት የምሥራች ደምሴ የአቶ ዳንኤል በቀለ እጮኛ እንደሆነችና በቅርቡም ተጋብተው ባለቤቱ እንደምትሆን ከቃለምልልሱ ለመረዳት ተችሏል። ከዚህም ሌላ ክሱን በዋነኛነት ይመራ የነበረውና “በሞት ፍርድ ይቀጡልኝ” እያለ ሲከራከር የነበረው ዓቃቤ ሕግ ሽመልስ ከማል ከአቶ ዳንኤል በቀለ ጋር የ20 ዓመት ጓደኛሞች እንደነበሩ በቃለምልልሱ ላይ ይፋ ሆኗል። አቶ ሽመልስ እና አቶ ዳንኤል ከዩኒቨርስቲ ወደ ሥራ እስከተሰማሩበት ጊዜ ድረስ፣ አንድ ማዕድ አብረው ቆርሰው፣ ያላቸውን ሣንቲም ለሁለት ተካፍለው አብረው በልተውና፣ አብረው ጠጥተው ከኢትዮጵያ እስከ እንግሊዝ አገር ዘልቀው፣ በአንድ አልጋ ላይ ተኝተው፣ የሆድ የሆዳቸውን ያወሩ ጓደኛሞች ነበሩ። ቃለምልልሱን ያደረገችላቸው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ስትሆን፤ እንቢልታ ጋዜጣ ያወጣውን ሙሉውን ቃለምልልስ እንደሚከተለው አቀርበነዋል።
|
|
Read more...
|
|
|
|
|
Thursday, 03 April 2008 23:59 |
|
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 26 ቀን 2000 ዓ.ም. April 4,2008)፦ አንጋፋው መምህርና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም በተለያዩ ገዳዮች ላይ በማተኮር በኢትዮጵያ ውስጥ በየሣምንቱ ከሚታተመው እንቢልታ ከተባለ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል ይህንን ታሪካዊ ቃለ ምልልስ በየሣምንቱ የሚያቀርብላችሁ ሲሆን፣ ዛሬ ፕሮፌሰሩ ከጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር በድርቅ ወይንም በፕሮፌሰሩ አጠራር በ”ችጋር” ጉዳይ ላይ ያደረጉትን ቃለምልልስ ይዘንላችሁ ቀርበናል። |
|
Read more...
|
|
|
|
|
|