ፍቅርና አንድነት ያለው ህዝብ ጠላቱን ያሸንፋል
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ባለፈው ሂትለርና የወያኔን መሪዎች ባነጻጸርኩበት ጽሁፍ ላይ መለስ ስብሀት በአማራው ህዝብ ላይ በሰፊው ሊያንቀሳቅሱ የሞከሩት እልቂት አንዴት በሚፈልጉት ልክ እንዳልገፋላቸው ሗላ ላይ እናወጋለን ብየ ነበር። በአለማችን ያሉ ጤናማ መንግስታት በዜጎቻቸው መካከል የመብት ልዩነትና የዘር የቀለም መለያየት፤ ግጭት እንዳይኖር ያለመታከት ይሰራሉ። ይተጋሉ። በኢትዮጵያ ያለው የዲያቢሎሶች መንግስት፤ ሰው በዘሩ ተለይቶ እንዲታወቅ፤ እንዳይስማማም እንዲበላላም ለማድረግ በትጋት ሲሰራ ሀያ ሁለት አመታትን አስቆጠረ።ወያኔ መቼ ይሆን እራሱን የሚያየው?
ይኸነው አንተሁነኝ
የታየው ድንገት የሚጠፋበት፣ የተፈለገው ለመድኃኒት ያክል እንኳ የሚታጣበት፣ ከኔ ጋር ነው ተብሎ የነበረው ሳይታሰብ የሚለይበትና ስምምነት የተደረሰበት ሳይቆይ የሚፈርስበት ወቅት። ሰዓታት ወቅቶችና ዓመታት ብቻ አይደሉም ትእይንቶችም እንደ ሸማኔ መወርወሪያ እየተምዘገዘጉ ነው። ጎን ለጎን ከአቻ የስልጣንና የደረጃ ጓደኛ ጋር፤ ከላይ ወደ ታች ወይም ከታች ወደ ላይ አለቃ ከምንዝር ምንዝር ካለቃ ሳይለይ የሚቧደኑበት የሚተሻሹበት የሚጓተቱበት ዘመን። ዘመነ ጭንቅ ንትርክ።
ታደሰ በዛብህ የመርካቶው አይጥ (ክፍል ሁለት)
በልጅግ ዓሊ
ክፍል ሁለት
“የተረፉት በሞቱት ይቀናሉ ...”
“Die Űberlebenden wereden die Toten beneiden ...”
ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘውን የመቃብር ቦታ ግቢ ውስጥ የሚገኝ አዳራሽ አለ። ዜጎቻችንን ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት አስከሬኑን ወደ ሃገራችን መላክ የተለመደ ቢሆንም፣ አንዳንዴ እንደ ሟች ወይም እንደ ሟች ቤተሰብ ፍላጎት የቀብሩ ሥነ ስርዓት እዚሁ ፍራንክፈርት ውስጥ ይፈጸማል።
የልጆቼ የጎህዬና የሱመያ፣ የሩቴና የኦማር “ጩኸት”
አብዩ በለው
ዓርብ ሴፕቴምበር 10 ቀን 2010 እ.ኤ.አ. ከሌሊቱ ለሰባት ሰዓት አስር ጉዳይ (12:50 AM) በኢሜል ለማገኛቸው የትየለሌ ወዳጆቼ ለ2003 ዓ.ም. የአዲስ አመት መልካም ምኞት መግለጫ የላኩላቸው መልዕክቴ የሚከተለው ነበር።
“መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ! እንኳዋን ከዘመን ዘመን በጤና አሸጋገራችሁ! እኔ ግን ከሃሌ ጋር እንዲህ ብያለሁ። ብርቱን ጥዬ አልሻገርም!”
የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ፎቶግራፎችና ፖስተሮች ይነሱ!
(ሪፖርተር ጋዜጣ በርዕሰ አንቀጹ)
የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያርፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ሠርቷል። በጋራ አዝኗል፣ አልቅሷል፣ ሸኝቷል። ዓለምም ተገርሟል። ተደንቋል።
የመለስ፣ የጳውሎስና የቀ.ኃ.ሥ ፋውንዴሽኖች
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
አዲስ ዘመን ጋዜጣ በጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም በፊት-ለፊት ገጹ ላይ የአንድን “አዋጅ መጽደቅ” ዜና አትሞ ነበር። ዜናው አዲስ አይደለም። “የአዋጁን በጆሮ” እንደሚባለው አይነት ነው። ከሁለት ቀናት በኋላ የወጣውም የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ ያንኑ ዜና ደግሞታል። ዜናውን ያነበበና የሰማ ሁሉ ወደአእምሮው የሚመጡበት ግዙፍ ጥያቄዎች አሉ። የእነዚህም ጥያቄዎች መሠረታቸው “ከፓርላማው ግልጽነት የጎደለው አሠራር” ጋር የተያያዙ ናቸው።
የኢትዮጵያ አምባገነኖች ጉም ይጨብጣሉ፣ አውሎ ነፋስን ይወርሳሉ
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)
የአፍሪካ አምባገነኖች የውሃ ላይ ቤተመንግስተና የውሃ ገደብ ለዘላለም ለስማቸው መጠሪያ ይሆናል ብለው ሲገነቡና ሲያስገነቡ ኖረዋል። ትተው ያለፉት በሕያውነት ጀግነውና ሲወደሱ መኖርን ነበር። ውጤቱ ግን ጉምን መጨበጥ ነፋስን መውረስ ሆኗል።
የህወሓት መሪዎች "የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መፃፍ አለበት!" ይላሉ፣ ለምን??
ገብረመድህን አርኣያ
ህወሓት ከጥንሥሱ ጀምሮ እንደተልዕኮ እና መመሪያው ለዘመናት ከብዙ የውጭ ወረራዎች እና ያልተሳኩ የቅኝ ግዛት ጥረቶች በአባቶቻችን ጽኑ ተጋድሎ የቆየውን ኢትዮጵያዊነት ለማፍረስ፤ ህዝብን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የቋንቋ እና የዘር ልዩነት ከፋፍሎ ለብቻው የትግራይን ሪፖብሊክ ለማቋቋም፤ ኤርትራን መገንጠል፤ ትግራይን ከአማራ ቅኝ ገዢዎች ነጻ ማውጣት፤ ኢትዮጵያ የምትባል በአጼ ምኒሊክ የተፈጠረችን አገር ከአለም ካርታ ላይ ማጥፋት፤ የሚሉ እና ሌሎች ዝርዝር ግቦችን እና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ድርጅት እንደነበር …
"በመለስ ሞት የተፈጠረውን ክፍተት ልንጠቀምበት ይገባል!" አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን
ከአቶ ግደይ ዘርዓፅዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ዋና ፀሐፊ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ
“የመለስ ሞት በስርአቱ ላይ የአመለካከት ወይም የአሰራር ለውጥን አላመጣም። አሁን ያሉት መሪዎች ግን ሥርዓቱን የመለስን ያህል ሊቆጣጠሩት አይችሉም። በውስጣቸውም የመከፋፈልና የስልጣን ፉኩቻ ፈጥሯል። ይህ ሁኔታ ለትግላችን አንዳንድ ቀዳዳዎችንና አመቺ ሁኔታዎችን ሊፈጥር ይችላል።”
አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን
33ቱ ፓርቲዎች ኢህአዴግን አስጠነቀቁ
(ፍኖተ ነፃነት ጥር 27 ቀን 2005 ዓ.ም.) 33ቱ ፓርቲዎች “ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ መግለጫ አወጡ። ኢህአዴግን አቋሙን እንዲያስተካክልም አስጠነቅቀዋል።
