ምነው ጠላቶች በዙብን?
ቸሩ ላቀው
እኛ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊነታችንና አንድነታችን ኩራታችንና ክብራችን ነው። እንኮራባቸዋለን፣ እንከበርባቸዋለን፣ እናከብራቸዋለን። ስንከበርበትና ስንኮራበትም ኖረናል። አንድ የአበባ ማስቀመጫ እንደ ምሳሌ እንውሰድ። በአበባው ማስቀመጫ ውስጥ የተለያዩ ቀለማት ያሉዋቸው አበቦች ይቀመጣሉ። የተቀመጡት አበቦች ለተመልካቾቻቸው ደስታን ይሰጣሉ። አዕምሮአቸውን ያረካሉ።
“ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቆች ሆነዋል ...” ስማቸው ያልተገለጸ እናት
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ሰሞኑን ከአገር ቤት አንዲት እናት ልጃቸውን ሊጠይቁ መተው ነበር። ልጃቸው የባለቤቴ ጓደኛ ነች። ... የኔም ጓደኛ! ... እኒህ አናት አንደበተ ርቱእና ተደምጠው የማይጠገቡ ጨዋታ አዋቂ ቀልደኛም ናቸው።
"የህወሓት/ኢህአዴግ የውስጥ ፍጥጫ፣ ዴሞክራሲን አይወልድም" ሸንጎ
Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. March 6, 2013)፦ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች (ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴን) አባላት ጅርጅታቸው ለረጅም ጊዜ ከተዘፈቁበት አረንቋ ውስጥ በማውጣት የሀገራችንን ክብርና የህዝባችንን መብት ያረጋገጠ መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ይታገሉ ዘንድ ሸንጎ መጠየቁን ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
እኛ - የመጨረሻዎቹ
ዳንኤል ክብረት
በፌስ ቡክ የተለቀቀ አንድ ጽሑፍ በምዕራቡ ዓለም የ1950ዎቹን፣ 60ዎቹን፣ 70ዎቹንና 80ዎቹን ትውልዶች በተመለከተ "እኛኮ በቶምና ጄሪ ፊልም ያደግን፣ በመንገድ ላይ የተጫወትን፣ በሬድዮ ካሴት ሙዚቃ ያዳመጥን የመጨረሻዎቹ ትውልዶች ነን።" ይላል።
አርቲስት በኃይሉ መንገሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አለምፀሐይ ወዳጆ
በኢትዮጵያ የትያትር ሙያ ተደናቂና ተወዳጅ የነበረው አርቲስት በኃይሉ መንገሻ በተወለደ በ57 ዓመቱ ማርች 3/2013 (የካቲት 24/2005) ዓ.ም. ነዋሪ ሆኖ በቆየበት በሰሜን አሜሪካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ከኬኒያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ምን እንማራለን?
ታምሩ ገዳ
ህዝባዊ ምርጫዎች በመጡ ቁጥር ስልጣኑን እነማን ይርከባሉ? ምርጫው ምን አዲስ ነገር ይፈጥርልን ይሆን? ምርጫው ሰላም ወይም አለመረጋጋት ... ወዘተ ይቀሰቀስ ይሆን? የሚሉ መሰል ጥያቄዎች በበርካታ መራጮች አይምሮ ውስጥ መመላለሱ የተለመደ ነው።
ቪቫ ኢትዮጵያ! ቪቫ ምኒልክ!

የአድዋው ድል
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የዐድዋ ጦርነት እስከዛሬ በአፍሪካም ምድርና በአፍሪካ ታሪክ ከተከናወኑት ጦርነቶች ከፍተኛውን የዋጋና የክብር ድልድል የያዘ ጦርነት ነው። አኒባል የአልፕን ተራሮች ዞሮ የአውሮፓን ኃያል መንግሥት ካሸነፈ ወዲህ፣ አንድ አውሮፓዊ ጦር በአፍሪካውያን ጦር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ስለሆነም፣ ጦርነቱ ብዙ መልክና ብዙ ቅጽል ተሰጥቶታል።
በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ዳዊት ፋንታ
ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍራንክፈርት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
በአባይ ግድብ ዙሪያ
ግርማ ካሳ
ቋጠሮ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ አንድ ቪዲዮ አየሁ። በሪያድ ሳውዲ አረቢያ፣ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢትዮጵያውያንን ጠርተው፣ በአባይ ግድብ ዙሪያ ባነጋገሩበት ወቅት፣ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ቪዲዮ ነው። «መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም»፣ «የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 27 ይከበር» የሚሉ መፈክሮች የተጻፉባቸው ነጭ ወረቀቶች ሲውለበለቡ ይታያሉ። ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ፣ ለአባይ ግንባታም በቂ ገንዘብ የተሰበሰበ አይመስልም።
የህወሓት ፍጥጫ ቀጥሏል
"አሁን ያለው ህወሓት ቆዳ ነው" እነ ስብሃት
"የህወሓት ወራሾች እኛ ነን" እነ አባይና አዜብ
ኢየሩሳሌም አርኣያ
ሁለት ቦታ የተከፈለው የህወሓት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም "መለስ ህወሓትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ህወሓት ቆዳ ነው።
