የትናንቷን እሁድ በወፍ በረር ስንቃኛት
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ዛሬ እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ነው። የዚህችን ዕለት ውሎየን ነው እንግዲህ የማካፍላችሁ። እኔም እንዳቅሜ የቤተሰቤን ፍላጎት አፍኜ አልጀዚራን ብቻ በመክፈት በማየው ነገር ሁላ በንዴት ስፎገላ ነው የትም ሳልሄድ ቤቴ ተከርችሜ የዋልኩ።
ዘጠኝ ቦላሌ ...
ይኸነው አንተሁነኝ
የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ህወሓት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም።
ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፭
ጽዮን ግርማ

"... እንዴት አድርጌ ደመወዜን እኮ አልሰጠችኝም፤ ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ እያለች ይኸው እስከ አሁን ታጉላላኛለች። ማታ ማታ በገባች ቁጥር እስከሚበቃት እነግራታለኁ፤ እርሷ መቼ ሰበብ ታጣለች። ቢጨንቀኝ ላገናኘኝ ልጅ ደውዬ ነገርኁት፤ ይብሱኑ እርሱም እኔም ያበደርኋትን አልከፈለችኝም አለኝ። ወይ አሜሪካ! ጉዷን አየኁላት።" መቼም መመረሯ መግለጫ የለውም። ...
ቋንቋ የህወሓት የጥፋት ሚዛን እና የመጭው ዘመን የኢትዮጵያዊያን ስጋት
ይኸነው አንተሁነኝ
ልቃቂት ነው ሂዎት፤ በእንዝርት ላይ እንደሚሽከረከረው የጥጥ ንድፍ ዘለላ እየተጠማዘዘ እየተሽመለመለ፣ እየጠበቀና እየላላ፣ እየተወጠረና እየረገበ የሚጠመጠም የሂዎት አንጓ። ያንዱ ሂዎት ዘርፍ በሌላው መሰረት ላይ እየተመጠነና እየተደረበ የሚከወን ኩነት።
ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፬
ጽዮን ግርማ
... አባ "አንድ ሰው ጨመርሽልና" አሏት ከትውውቃችን አስቀድሞ አብረው እንዳዩን። "ኧረ ተመላሽ ናት አባ፤ ለሥራ ነው የመጣችው" አለቻቸው። "ትዳር መሥርተሻል?" ጠየቁኝ። "አዎን አባ ቆይቻለኹ" አልኋቸው። ሣቅ አሉና "እኔ ደግሞ ገና ከሩቁ ሳይሽ ልድርሽ እያሰብኹ ነበር፤" አሉኝ ሐሳባቸው ያለመሳካቱ የፈጠረባቸውን ስሜት በፈገግታቸው እየሸፈኑ። ...
የክሽፈት እንጉርጉሮ፣ ታሪክ ላይ ተሸንቅሮ!
ካሣሁን ዓለሙ
"አንድ ሰው በአደባባይ ሲናገርም ሆነ ጽሑፍ አሳትሞ ሲያሰራጭ ራሱን አጋልጦአል፤ የተናገረው ወይም የጻፈው መቶ በመቶ ያህል በራሱ ጉዳይ ላይ ብቻ ከሆነ፣ የመተቸት ወይም ሐሳብ የመስጠት ግደታ የለብንም፤ ነገር ግን የተናገረው ወይም የጻፈው በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ከሆነ፣ የዚያ አገር ዜጋ ሁሉ በጉዳዩ ውስጥ የመሳተፍና ሐሳቡን በሙሉ ነጻነት የመስጠት መብት አለው።"
(ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም፣ መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ፣ ገጽ78-79)
ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፫

ጽዮን ግርማ
... ፀጉሯን በፋሽን የተቆረጠች፣ ቀጭን ዝንጥ ያለች ልጅ ቦርሳዋን በአንድ እጇ አስገብታ በአንድ እጇ የስታር ባክስ ቡናዋን እንደያዘች ከአሳንሳሩ ወጣች። የፋሽን ትርኢት በምታሳይ ሞዴል አረማመድ በሽቶዋ አውዳን፣ ማስቲካዋን እያላመጠች በአጠገባችን እልፍ አለች። ከሴቶች ማጌጫ የቀራት ነገር አለ ማለት አይቻልም። እኔ "ልጅቷ" አልኳት እንጂ እሷ እንኳን "ልጁ" ነበረች። በጣም ተገርሜ "ወንድ ነው አይደል?" ስል ወ/ሮ ሐረገወይንን ጠየቅኋት። "አዎ፤ ወንድ ነው፣ ግን ደግሞ ሚስት ነው" አለችኝ። መጸየፏ ከፊቷ ያስታውቃል። ...
የፋሽስቱ ግራዚያኒን ሐውልት መሠራት ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ በአ.አ. ታሰሩ
”ይህ የጤንነት አይመስለኝም!” ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
Ethiopia Zare (እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. March 17, 2013)፦ የፋሽስቱን ግራዚያኒ ሐውልት በጣሊያን ሀገር በመሠራት ላይ መሆኑን በመቃወም በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ከ35 በላይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ። ከእነዚህም ውስጥ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ይልቃል ጌትነት ጨምሮ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አመራር አባላት በዛሬው ዕለት ታስረዋል።
ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ - መልክአ ኢትዮጵያ - ፪

ጽዮን ግርማ
... በርካቶች ሥራ ፍለጋ በሚሰደዱባት የዓለም ቁንጮ በሆነችው ሀገረ አሜሪካ፣ ገላቸውን ለሽያጭ ላቀረቡት ወጣት እንስቶችስ "አይ የእንጀራ ነገር" ስል ደረቴን ልድቃላቸው ይሆን? ጉዳዩ የእንጀራ አይመስልም፤ እናም ደረት የመድቃቱ ነገር አስፈላጊ አልመሰለኝም። ...
