Home ዋና ገጽ

የ2002 ምርጫ ቀርቧል፤ ኢህአዲግ ጥበቃውን እያጠናከረ ነው Print E-mail

Ethiopia Zare (ሐሙስ መጋቢት 2 ቀን 2002 ዓ.ም. March 11, 2010)፦ ለምርጫው የሁለት ወር ከ15 ቀናት ዕድሜ ቀርቷል። በአዲስ አበባና በተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች የኢህአዲግ መንግሥት ልዩ ወታደራዊ የጥበቃ ኃይሎችን እያሰማራ መሆኑ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ቢያንስ ዶሮዋን አንሆንም? Print E-mail

Dorowaኩችዬ - መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. (ማርች 10 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.)

ሹም መሆን ብዙ ፈተና አለው ወዳጄ! አንዲት አነስተኛ ወረዳ ውስጥ አስተዳዳሪ ሆኖ የተመረጠ ሰው የህዝቡን ተሳትፎ ለማግኘት ቁርጥ ሃሳብ ያደርጋል። የነጋዴው፤ ያስተማሪው፤ የተማሪው፤ የገበሬው በር አልቀረውም። የሁሉንም አንኳኳ። አንዱን ቀን እግሩ ካንድ ገበሬ ቤት ይጥለውና ... 

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ኢንጂንየር ግዛቸውና አቶ ስዬ ወደ መቀሌ ያመራሉ Print E-mail

‘ዘመቻው ተጧጡፎ ቢቀጥልም መድረኩም ሆነ ዓረና ከምርጫው አይወጡም’ አቶ ገብሩ አስራት

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ ኢንጂንየር ግዛቸው እና አቶ ስየ አብርሃ ወደ መቀሌ የሚያመሩት እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. መድረክ በትግራይ በሚያደርገው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ተሳትፎ ለማድረግና በትግራይ ክልል የድርጅታቸውን የምርጫ ሂደት ለመከታተል መሆኑን በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጠቆሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

በመብራት መቋረጥ ምሬት እየጨመረ ነው Print E-mail
Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ የግልገል ግቤ ቁጥር ሁለት ከተመረቀና ሥራ ከጀመረ በሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመብራት መቋረጥ ህዝብ እየተማረረ መሆኑ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

አቶ ስየ አብርሃ ለቢቢሲው ዘገባ ምላሽ ሰጡ - ‘ዝም ብዬ አልቀመጥም’ ሲሉ ተደምጠዋል Print E-mail

“ባይጫኑን! ባይገፉን! ጥሩ ነው፤ ከተጫኑን ግን ሁሉን ነገር ይፋ እናወጣዋለን!” አቶ ስየ አብርሃ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ አቶ ስየ አብርሃ እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አሁንም በመከላከያ ሚኒስትርነትና በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉት የነበረውን የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ ከመንቀፋቸውም በላይ አቶ ስየ አብርሃ ከፍተኛ ትኩረት ለሳበው የቢቢሲ ዘገባ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

መድረክ ህዝባዊ ስብሰባውን እያካሄደ ነው Print E-mail

የመድረክ የካቲት 28 ቀን 2002 ዓ.ም. ህዝባዊ ስብሰባ“ህዝቡ ፈርቶና ተሸማቆ መኖር የለበትም” የመድረኩ አመራር

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. March 10, 2010)፦ ህዝቡ ለነፃነቱ መስዋዕትነት መክፈል እንደሚኖርበት እና ፈርቶና ተሸማቆ መኖር እንደሌለበት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት መድረክ (መድረክ) የካቲት 28 ቀን ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ብራቮ! አበራ ለማ (የትዝታ ቅምሻ) Print E-mail

ስሜነህ ታምራት ከስዊድን

ከአዲስ አበባ ተነስተን ወደ ወሊሶ በሎንቺና ስጓዝ ነበር፤ ለመጀመሪያ ጊዜ አበራ ለማን ያገኘሁት። እናም “ኩል ወይስ ጥላሸት” የሚል መጽሐፍ በገፀበረከት አበረከተልኝ። “የማን መጽሐፍ ነው?” አልኩት፤ “እኔ የሞካከርኳት መጽሐፌ ናት” አለኝ - ለስለስ ባለ አንደበት። አመስግኜ ተቀበልኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ለኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው Print E-mail

ወዶ የዋጡትቅልጥም ከፍርምባ ይጥም

ታምራት ታረቀኝ

ከኢ/ር ግዛቸው ጋር ለመጨረሻ ግዜ ተገናኝተን የተነጋገርነው ሰኔ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በእኔ ጠያቂነት በርሳቸው ቢሮ ውስጥ ነው። ከቀትር በኋላ። ርሳቸው ጋር ለመነጋገር ምክንያቶቼ ሁለት ነበሩ። አንደኛው ሰኔ 8 እና 9 በነበረው የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በሌሎች ሰዎች እየተመሩ ስህተት ሲፈጽሙ ማየቴ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ዋና ፀሐፊ አስራት ጣሴ ከኃላፊነት በመሸሽ በምክትላቸው ወጪ የሚያደርጉዋቸው ደብዳቤዎች ጉዳይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የኖርዌይ ደራስያን ማኅበር ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅን የ2009 ዓ.ም. ተሸላሚ አደረገ Print E-mail

Playwright, writer & journalist Dawit Issak ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅማትያስ ከተማ ከስቶክሆልም

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. March 5, 2010)፦ ከተመሰረተ ከመቶ ዓመት ዕድሜ በላይ ያስቆጠረውና ብዙ እውቅ ደራስያንና ጋዜጠኞችን በላቀ የሥራ ውጤታቸው ሲሸልም የቆየው የኖርዌይ ደራስያን ማኅበር፤ የ2009 (እ.ኤ.አ.) ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ሽልማቱን ስዊዲሽ-ኤርትራዊ ለሆነውና በኤርትራ በእስር ላይ ለሚገኘው ፀሐፊ ተውኔት፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅ ሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የመለስ ዜናዊ ገደብ አልባነት Print E-mail

ካሕሳይ በርኸ እና ተስፋይ አፅብሃ (የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. / ማርች 5 ቀን 2010)

መለስ የህወሓት 35ኛውን ዓመት አስመልክቶ ሲናገርና በድምፅ ወያነ ትግራይ ጥያቄዎች ቀርበውለት ሲመልስ ልዩ ክብደት የሚሰጣቸው የቅስቀሳ መልዕክቶች አሉ። አንዱ መልዕክት በሃሳቦች ላይ ሳይሆን በሰዎችና ድርጅቶች እንዲሁም በተሸፋፈነ መልክ በህዝብ ላይ ያነጣጠረ አስቀያሚ፣ መጥፎ አርኣያነት ያለውና ባህላችንን የሚበክል ስድብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በሃሳቦች ላይ ያተኮረ የሚመስል ነገር ግን ሃሳቡ የተቃዋሚዎች መሆኑን ማስረጃ ሳይቀርብለት በእነሱ ያልተባለን እንደተባለ አድርጎ የሚያቀርበው በውሸት ላይ የተመሰረተ ህዝብን የማወናበድና የማስፈራራት ቅስቀሳ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 
«StartPrev12345678910NextEnd»

Page 1 of 88
 
Banner
Ethiopian-Eritrean Friendship Conference, San Jose March 12-14

Memorial for Abune Zena Markos