ታሪክ

የገና በዓል በዘመነ ዮሐንስ (ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ) Print E-mail
User Rating: / 3
PoorBest 

እንኳን ለዘመነ ዮሐንስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ልደት የሚከበረው በታኅሣሥ 29፥ በሠግር ዓመት ግን በታኅሣሥ 28 ስለሆነ ዘንድሮ የሚከበረው በታኅሣሥ28 ቀን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የደመራ ታሪክ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ) Print E-mail
User Rating: / 10
PoorBest 

ደመራ በኃይማኖታችን፣ በታሪካችን እና በባሕላችን አንጻር

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it መስከረም ፳፻፬ ዓ.ም.

‘ደመራ’ ደመረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው። ትርጉሙ ጭመራ ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው። ጥሪት (ካፒታል) እንዳይጎድል እንዳይቀነስ ይልቁንም እየበዛና እያደገ እንዲቀጥል ጠብቆ መያዝ የሚያስችል ደመራ ነው። ስሙ እንደሚያመለክተው ማስታወሻነቱ ለተጠራቀመ፣ ለተሰበሰበና ለተጨመረ ነገር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የጣልያን ውድቀት (ጌቱ) Print E-mail
User Rating: / 9
PoorBest 

የጎንደር ጦርነት የአርበኞች ድል የፋሽስት ጣልያን የመጨረሻ ውድቀት

ኃብተሥላሴ ስለሺ (ጌቱ) ከፓሪስ - ፈረንሣይ

ወራሪው የፋሽስት ጣልያን ጦር በጀግኖች አርበኞች ተጋድሎና በእንግሊዝ ረዳትነት ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ድል ሆኖ አዲስ አበባን ከለቀቀ በኋላ፤ የተቀረው የጠላት ጦር የምስራቅ አፍሪካ የጣልያን ጦር የበላይ አዛዥ በሆነው በዱክ ዲዎስታ አመራር ስር ደሴ ላይ መሽጎ ሲጠባበቅ፤ የቀረው ጦር እንዲሁ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ጦር አዛዥ በሆነው በጄኔራል ናዚ አመራር ጎንደር ላይ መሽጎ የሙሶሎኒን እርዳታ ይጠባበቅ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የዓድዋ ድልና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ Print E-mail
User Rating: / 6
PoorBest 

የዓድዋ ድልና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ድርሻና ውለታ

ፍቅር ለይኩን ከደቡብ አፍሪካ

የዓድዋ ድልን በማስመልከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን በስንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ በማኅበረ ቅዱሳን የምርምርና የጥናት ማእከል ድሉን አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ የነበራትን ሚና ለማዘከር በአዲስ አበባ በብሔራዊ ሙዚየም የተደረገውን ውይይት ዜና በደጀ ሰላም ማንበቤ በውስጤ አንድ ስሜት አጫረብኝ፤ እናም ስለ ድሉና ቤተ ክርስቲያናችን ስለነበራት ታላቅ ድርሻና ወለታ ጭምር ጥቂት ለመጨመር አስብኩና ብዕሬን አነሳሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ዝክረ አድዋ በኪነጥበብ መወድስ (ዳንኤል አበራ) Print E-mail
User Rating: / 16
PoorBest 

ዳንኤል አበራ ( This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it )

ኢትዮጵያ ከዘመነ መሣፍንት ተላቅቃ አንፃራዊም ቢሆን ወደ ተረጋጋ ማዕከላዊ አስተዳደር የተሸጋገረችበት ዘመን። አባ ዳኘውም እምዬም እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ ሥልጣን ያደራጁበት እና ኢትዮጵያን ያሰሱ አውሮፓውያንን ባላሰለሰ የመሣሪያ ስጦታም ግዢም ጥያቄ የወተወቱበት ዘመን፤ ኋላም ተክለፃዲቅ መኩሪያ እንደጻፉልን “ባመጣው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ” ከተባለበት የጣሊያን መንግሥት ጭምር የመሣሪያ ስጦታ ተረክበው ምኒልክ ጦራቸውን ያደራጁበት ዘመን፤ አውሮፓውያን አህጉራትን እንደቅርጫ ሥጋ የተከፋፈሉበት ዘመን። አፍሪካም፣ ኢትዮጵያም የዚህ ዕጣ ፈንታ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በዝግ ተወስኖ ለአፄ ምኒልክና መንግሥታቸው መልዕክት የተነገረበት ዘመን፤ አፄ ምኒልክም መልዕክቱን ሰምተው እግዜር ይስጥልኝ ውሳኔያችሁን አልቀበልም ያሉበት፣ የጦርነትም ስጋት ያንዣበበት ዘመን ነበር ዘመኑ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 
«StartPrev12NextEnd»

Page 1 of 2

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!