ታሪክ
99 ቀናት በአዲስ አበባ
ጋዜጠኛው ኤን. ማንጄላ (N. Mandela) በኢትዮጵያ
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በታኅሣሥ አጋማሽ 1954 ዓ.ም በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደረገለትና በጥር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ገባ። ይህ ሰው በሦስት ወራት ከአንድ ሳምንት (በ98 ቀናት) ቆይታው ወቅት እጅግ የተጣበበ መርሐ ግብር እንደነበረበት ያስታውቃል።
ቪቫ ኢትዮጵያ! ቪቫ ምኒልክ!

የአድዋው ድል
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የዐድዋ ጦርነት እስከዛሬ በአፍሪካም ምድርና በአፍሪካ ታሪክ ከተከናወኑት ጦርነቶች ከፍተኛውን የዋጋና የክብር ድልድል የያዘ ጦርነት ነው። አኒባል የአልፕን ተራሮች ዞሮ የአውሮፓን ኃያል መንግሥት ካሸነፈ ወዲህ፣ አንድ አውሮፓዊ ጦር በአፍሪካውያን ጦር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ስለሆነም፣ ጦርነቱ ብዙ መልክና ብዙ ቅጽል ተሰጥቶታል።
አስሩ የጽልመት ቀናት በኢትዮጵያ
(ከየካቲት 8/1929 - የካቲት 17/1929 ዓ.ም)
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በመስከረም 1927 ዓ.ም የወጣው Detroit Times — (Sept. 22, 1935, p. 3) መጽሔት ከአንድ ታላቅ ሳይቲስትና የፈጠራ ባለሙያ ጋር የኢትዮጵያንና የጣሊያንን ወረራ አስመልክቶ ቃለ-ምልልስ አድርጎ ነበር።
“የኢትዮጵያና የሕዝቧ ደመኛ ...” ይሰቀል!
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
በ1900 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግሥታት ስምምነት፣ “በልዩ የቆመ ፍርድ ቤት” የሚል ስያሜ የተቋቋመ ፍርድ ቤት ነበር። ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ሥራውን በ1914 ዓ.ም. ሲጀምር፣ የመጀመሪያው የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደ ሥላሴ ነበሩ። ከርሳቸውም ቀጥለው የተሾሙትም ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ናቸው። የዚህ ፍርድ ቤት ዋነኛው ተግባር የውጭ ዜጎች እርስ-በራሳቸው ሲጋጩና/ወይም የውጭ አገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በተጋጩ ወይም በተካሰሱ ጊዜ ፍርድ መስጠት ነበር።

