ዋና ገጽ
 
እንቁጣጣሽን ከቤተሰብዎ ጋር በስቶክሆልም ከእኛ ጋር ያሳልፉ! Print E-mail
User Rating: / 3
PoorBest 

እንቁጣጣሽን ከቤተሰብዎ ጋር በስቶክሆልም ከእኛ ጋር ያሳልፉ!

ልዩ የአዲስ ዓመት የመዝናኛ ዝግጅት በስቶክሆልም ከተማ

የኢትዮጵያን አዲስ ዓመትና በስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮ ምስረታን 17ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መስከረም 1 ቀን 2003 ዓ.ም. (ሴፕቴምበር 11 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) ከቀኑ 7፡00 (13፡00) ሰዓት ጀምሮ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት ይደረጋል።

 

የመዝናኛ ዝግጅቱ በቡፌ ምሳንና በባህላዊ የቡና አፈላል ይጀምራል። በዝግጅቱ ቲያትር፥ ባህላዊ የልብስ ትርዒት (ፋሽን ሾው)፥ የልዩ ተሰጥዖ (ታለንት ሾው) ፕሮግራሞች የተካተቱበት ሲሆን፣ ድምጻውያን ይድነቃቸው ተፈሪ እና መስከረም ሀብታሙ እስከንጋቱ 11፡00 (5፡00) ሰዓት ድረስ የሚቆይ የሙዚቃ ምሽት ይዘውላችሁ ይቀርባሉ።

 

እርስዎና ልጆችዎ የዚህ ዝግጅት ተካፋይ በመሆን በስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮን ይርዱ።

 

በክብር እንግድነት

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት)

ወ/ሮ ቫኛ ሉንድቢ ቬደን (የስዊድንና የወቅቱ የአውሮፓ ሠራተኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት) ይገኛሉ።

 

የዝግጅቱ አድራሻ፦

አልቢ በሚገኘው SUBTOPIA

Rotemannav. 10, 145 57 NORSBORG

(ካርታውን አሳየኝ)

http://www.hitta.se/ViewDetailsPink.aspx?Vkiid=ZZ868HbHqqOEt6%252f5KN0Npw%253d%253d&vad=SUBTOPIA  

የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ  

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!